Skip to content
Facebook Twitter
  • አማርኛአማርኛ
  • EnglishEnglish
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • ስለ እኛ
    • ስለ ተቋማችን
    • ስለ ባልደረቦቻችን
    • ከእኛ ጋር ለመስራት
    • አግኙን
  • ክልሎች
        • ክልሎች

          ኢሰመኮ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ማስከበርና መጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው ራሱን የቻለ የፌዴራል ተቋም ነው።

        • አዲስ አበባ
        • አፋር
        • አማራ
        • ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ
        • ኦሮሚያ
        • ደቡብ ክልል
        • ሶማሌ
  • የስራ ዘርፎች
        • የስራ ዘርፎች

          እኛ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን የማስፋፋት እና የማስጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠን ገለልተኛ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም ነን
        • የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ መብቶች
        • የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች
        • የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች
        • የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን መብቶች
        • የሰብአዊ መብቶች ትምህርት
        • የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ
        • የሴቶች እና ሕጻናት መብቶች
  • ጋዜጣዊ መግለጫ
  • ሪፖርት
  • ሚዲያ
    • ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
    • የኢሰመኮ ቪዲዮዎች
    • የኢሰመኮ ጽሑፎች
  • ተጨማሪ መረጃዎች
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርስ እንግልት፣ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስርና ጥቃት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል

July 16, 2021July 21, 2021 ጋዜጣዊ መግለጫ

የዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችና የሰብአዊ መብቶች መርሆች በግጭት ወቅት ጭምር ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ የሚያዙና ሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች ላይ ከፍ ያለ ግዴታ የሚጥሉ ናቸው

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ በሲቪል ሰዎች ላይ እንግልትና እስር፣ የንግድ ቤት መዘጋት፣ ብሎም በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መከሰቱንና ሕይወት መጥፋቱን፣ እንዲሁም በታሳሪዎችና በምርኮኞች ላይ የሚደርስ ኢሰብአዊ አያያዝ፣ በስደተኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ሕጻናትን ለውትድርና መጠቀም የሚያመላክቱ መረጃዎች እጅግ የሚያሳስበው መሆኑን ገለጸ።

ሐምሌ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ፎገራ ወረዳ፣ ወረታ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በአካባቢው ነዋሪዎች የሆኑ ሦስት የትግራይ ተወላጆች በድንገት በተሰባሰቡ ነዋሪዎች በደረሰባቸው ድብደባ መገደላቸው ለኮሚሽኑ የደረሱት ጥቆማዎች ያመለክታሉ።

ይህ ጥቃት የደረሰው ከእለቱ አንድ ቀን አስቀድሞ ፍየል ውሃ በሚባል ቦታ ሕወሃት/ትግራይ መከላከያ ኃይሎች በወሰዱት የጥቃት እርምጃ የፎገራ ወረዳ ነዋሪዎች የሆኑ የሚሊሽያ ቡድን አባላትና የወረዳው የሰላምና ፀጥታ ኃላፊ መገደላቸው ከተነገረ በኋላ ነው። ሐምሌ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ረፋዱን ጉመራ ወንዝ ተብሎ ከሚጠራና ከተገደሉት የወረዳው የሰላምና ፀጥታ ኃላፊ ትውልድ ቦታ የኃላፊውን እሬሳ ለመቀበል የመጡ ነዋሪዎች ጥቃቱን እንዳደረሱ ይነገራል።

የፎገራ ወረዳና የአካባቢው የፀጥታና የአስተዳደር ኃላፊዎች በወሰዱት አፋጣኝ እርምጃ ሁኔታው የተረጋጋና ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ቢሆንም፣ የተከሰተው ሁኔታ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እንዳይዛመት የሚያሰጋ ነው።

በትግራይ ክልል በሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ላይና የሕወሃት/ትግራይ መከላከያ ኃይሎች ተቃዋሚ ናቸው በሚል በሲቪል ሰዎች ላይ እንደተወሰዱ የሚነገሩ የግድያና የአፈና እርምጃዎች የሚያሳስቡ ናቸው። ከአላማጣና አካባቢው በድጋሚ ያገረሸውን ግጭትና በመኾኒ እየተወሰዱ ስለመሆናቸውን የሚነገሩ የበቀል ጥቃቶች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰዎች መፈናቀል እያደረሰ ነው።

ቴሌኮሙኒኬሽንና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መቋረጣቸው የሰብአዊ መብቶች ክትትል ስራውን አዳጋች ያደረገው ቢሆንም፣ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ያለውን የተደራሽነት ሁኔታ በተመለከተ የሚያደርገውን ክትትል የሚቀጥልና በቆቦ፣ በወልዲያ እና በማርሳ ተጠልለው የሚገኙ ከአላማጣና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎችን የሚጎበኝ መሆኑን ይገልጻል።

ኢሰመኮ የግጭቱ መባባስና የግጭቱ ተጽእኖ በአፋርና በአማራ ክልል የሚገኙ ቦታዎችን ጨምሮ ወደ ትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ጭምር መስፋፋቱ እጅግ የሚያሳስበው ነው።

እንዲሁም ኮሚሽኑ አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚደርሱትንና በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚደርሱ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስር፣ የንግድ ቤት መዘጋት እና የእንግልት መረጃዎችንም እየተከታተለ ይገኛል። የሚድያ ሰራተኞችን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ ሌሎች ቦታዎች እየተወሰዱ መሆናቸውን ለኮሚሽኑ ጥቆማዎች ደርሰውታል።ከሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተባብሶ የታየው ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ ክስተትና እስር ሁኔታ ተገቢውን ትኩረትና መፍትሔ ከአለማግኘቱ በተጨማሪ፤ በስፋት የሚደመጡ የጥላቻና ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች ሁኔታው ሊያባብሱና ብሎም በማኅበረሰቦች መካከል ያለውን ትስስር ሊያላሉ የሚችሉ ናቸው። ስለሆነም፣ በየትኛውም አካባቢ ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ ነዋሪዎች በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቁና የፌዴራል መንግስትም ሆነ የክልል መስተዳድሮች በነዚህ ነዋሪዎች ላይ እንግልት ያደረሱና ሌሎች ሕገወጥ ድርጊቶች የፈጸሙ የሕግ አስከባሪ አካላትን ሕግ ፊት ሊያቀርቡ ይገባል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “በተለይም ይህን በመሰል ፈታኝና የውጥረት ወቅት መንግስት ለሲቪል ሰዎችና ተጋላጭ ለሆነው ማኅበረሰብ ክፍል ከፍተኛ ጥበቃ የማድረግ ተጨማሪ ኃላፊነት የሚጣልበት ጊዜ ነው። መሰረታዊ የሆኑ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችና የሰብአዊ መብቶች መርሆች በግጭት ወቅት ጭምር ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ የሚያዙና ሲቪል ሰዎችና የሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች ላይ ከፍ ያለ ግዴታ የሚጥሉ ናቸው። ስለሆነም ኮሚሽናችን በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን ጨምሮ አጠቃላይ ሁኔታውን በተመለከተ የሚያደርገውን የክትትል ስራ የሚቀጥል ሲሆን፣ በግጭቱ ለሚሳተፉ ወገኖች በሙሉ እንዲሁም የሚድያ ተቋማትን ጨምሮ ለሀገራዊና ለዓለም አቀፍ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በሙሉ ማንኛውንም የማኅበረሰብ ክፍል አደጋ ላይ ከሚጥል ንግግር፣ መግለጫዎችና ተግባራት እንዲቆጠቡ ኢሰመኮ ጥሪ ያቀርባል” ብለዋል።

Reports & Press Releases

June 7, 2021June 7, 2021 ሪፖርት
ብዛት ያላቸው ተፈናቃዮች ከግንቦት 16 ቀን 2013 ጀምሮ በጸጥታ ኃይሎች ተይዘዋል
March 8, 2021May 11, 2021 ጋዜጣዊ መግለጫ
በምርጫ ሂደቶች የሚሳተፉ ሴቶችን ከጥላቻ ንግግር እና ጾታዊ ጥቃት መከላከል ይገባል
November 24, 2020May 30, 2021 ሪፖርት
በትግራይ ክልል፣ አክሱም ከተማ የተፈጸመው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርት
November 24, 2020May 21, 2021 ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በማይካድራ የተፈጸመው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፈጣን ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርት

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup

Signup for the Latest Update from EHRC

    Submit your email here to get the latest update from EHRC.

    Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

    ጠቃሚ ድረ-ገጾች

    • NANHRI
    • GANHRI
    • OHCHR
    • ACHPR

    ተሳተፉ

    • ከእኛ ጋር ለመስራት
    • አግኙን

    ከእኛ ጋር ይገናኙ

    • Facebook
    • Twitter
    • LinkedIn
    • YouTube
    EHRC
    እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶችን የማስተዋወቅ እና
    የማስጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠን ነፃ ብሄራዊ የሰብአዊ መብቶች
    ተቋም ነን
    Submit your email to get the latest update from EHRC

    © 2022 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

    ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎት ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።

    ኩኪዎችን መጠቀም ላይ መስማማትዎን እባክዎ ያሳውቁን።

    Scroll to top
    • የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)
    • ስለ እኛ
      • ስለ ተቋማችን
      • ስለ ባልደረቦቻችን
      • ከእኛ ጋር ለመስራት
      • አግኙን
    • ክልሎች
      • አዲስ አበባ
      • አፋር
      • አማራ
      • ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ
      • ሶማሌ
      • ደቡብ ክልል
      • ኦሮሚያ
    • የስራ ዘርፎች
      • የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ መብቶች
      • የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች
      • የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች
      • የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን መብቶች
      • የሴቶች እና ሕጻናት መብቶች
      • የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ
      • የሰብአዊ መብቶች ትምህርት
    • ጋዜጣዊ መግለጫ
    • ሪፖርት
    • ሚዲያ
      • ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
      • የኢሰመኮ ቪዲዮዎች
      • የኢሰመኮ ጽሑፎች
    • ተጨማሪ መረጃዎች
    • አማርኛአማርኛ
    • EnglishEnglish
    Facebook Twitter
    Search
    Powered by  GDPR Cookie Compliance
    Privacy Overview

    This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

    Strictly Necessary Cookies

    Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

    If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.