Skip to content
Facebook Twitter
  • አማርኛአማርኛ
  • EnglishEnglish
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • ስለ እኛ
    • ስለ ተቋማችን
    • ስለ ባልደረቦቻችን
    • ከእኛ ጋር ለመስራት
    • አግኙን
  • ክልሎች
        • ክልሎች

          ኢሰመኮ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ማስከበርና መጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው ራሱን የቻለ የፌዴራል ተቋም ነው።

        • አዲስ አበባ
        • አፋር
        • አማራ
        • ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ
        • ኦሮሚያ
        • ደቡብ ክልል
        • ሶማሌ
  • የስራ ዘርፎች
        • የስራ ዘርፎች

          እኛ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን የማስፋፋት እና የማስጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠን ገለልተኛ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም ነን
        • የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ መብቶች
        • የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች
        • የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች
        • የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን መብቶች
        • የሰብአዊ መብቶች ትምህርት
        • የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ
        • የሴቶች እና ሕጻናት መብቶች
  • ጋዜጣዊ መግለጫ
  • ሪፖርት
  • ሚዲያ
    • ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
    • የኢሰመኮ ቪዲዮዎች
    • የኢሰመኮ ጽሑፎች
  • ተጨማሪ መረጃዎች
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ትግራይ ክልል ፡ የሲቪል ሰዎችን ሁኔታ ለማሻሻል አፋጣኝ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል

July 14, 2021February 17, 2022 ጋዜጣዊ መግለጫ

በክልሉ የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መመለስና በትግራይ ክልል ስላለው ተጨባጭ የፀጥታ ሁኔታና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት በቂ መረጃ መስጠት፣ በዚህ ረገድ ያሉ ክፍተቶችን ለማረምና የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ትብብር ለመፍጠር ቀዳሚ እርምጃዎች ናቸው

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም ማወጁን ተከትሎ የግንኙነት መሰመሮች በመቋረጣቸው፣ በክልሉ ነዋሪዎች የሚገኙበት ሁኔታ እንደሚያሳስበውና መንግስት የነዋሪዎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ የሚረዱ እርምጃዎች በአፋጣኝ ሊወስድ እንደሚገባ ገለጸ። በክልሉ የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መመለስና በትግራይ ክልል ስላለው ተጨባጭ የፀጥታ ሁኔታና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት በቂ መረጃ መስጠት፣ በዚህ ረገድ ያሉ ክፍተቶችን ለማረምና የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ትብብር ለመፍጠር ቀዳሚ እርምጃዎች ናቸው።

ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ የሚደረገው ጥረት አስፈላጊነት እንደተጠበቀና በክልሉ ለሚደረጉ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቶች ጥበቃና ለተደራሽነቱ ትብብር እንደሚቀጥል መገለጹ የሚበረታታ ሆኖ፣ የሲቪል ሰዎች ደኅንነትና ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛዎቹ የትግራይ አከባቢዎች የመብራት፣ የስልክ እና የውሃ አገልግሎት በመቋረጡ በክልሉ ነዋሪዎች ላይ ከባድ የኑሮ ጫና እያስከተለ ይገኛል። የባንክ አገልግሎት መቋረጥና የጤና አገልግሎት አቅርቦትና ተደራሽነት ውሱንነት ችግሩን አባብሶታል።

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሀገራዊና ዓለምአቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ እና የስልክ አገልግሎት መቋረጥን ጨምሮ የሌሎች አቅርቦቶች እጥረት የሰብአዊ ድጋፉን በከፍተኛ ደረጃ እንደጎዳውና በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ስደተኞች ስለሚገኙበት ሁኔታ ማወቅ አስቸጋሪ እንዳደረገው ይገልጻሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ ነዋሪዎችና የሚዲያ ሰዎችን ጨምሮ፣ ሌሎች ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎችን ሁኔታ ኮሚሽኑ በመከታተል ላይ ይገኛል። ይህም በነዋሪዎች ላይ ማንነትን በመለየት ለጥርጣሬ እና መድልዎ የሚያጋልጥ ተግባር እንዳይሆን ስጋት የሚያሳድር ነው።

በተጨማሪም፣ በክልሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ወጣቶች ወላጆችና ቤተሰቦች ተማሪዎቹ በአሁኑ ወቅት ስለሚገኙበት ሁኔታ ተገቢው ምላሽ እና ማብራሪያ እንዲሰጣቸው የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የነዋሪዎችን ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግስት ግዴታ መሆኑን አስታውሰው፣ “በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎች ስላሉበት ሁኔታ የተገቢው መረጃ ማነስ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከሚደመጡ ዘገባዎችና ንግግሮች ጋር ተዳምሮ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ የሚጥል ነው። የተኩስ አቁሙ በሁሉም በግጭቱ ተሳታፊ በነበሩ ወገኖች ሁሉ በቁርጠኝነት መከበር እና የመሰረታዊ አገልግሎቶች በአፋጣኝ መመለስ፣ አጠቃላይ ሁኔታውን ለማሻሻል፣ በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ችግር ዘላቂ መፍትሔ ለማፈላለግ፣ እንዲሁም ሰብአዊ አቅርቦቱ እንዳይቋረጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው። በተጨማሪም ማንኛውም አይነት እስር ሁልጊዜም ሕጋዊ ሥርዓትን የተከተለ ሊሆን ይገባል” ብለዋል። ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ሁሉ ሁኔታውን የሚያባብሱ፣ በሕዝቦች መካከል ጥላቻና ጥርጣሬን ሊፈጥሩ ከሚችሉ ንግግሮች እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል።

Reports & Press Releases

June 18, 2021July 13, 2021 ጋዜጣዊ መግለጫ
በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብአዊ መብቶችን አክብረው መንቀሳቀስ አለበቸው
June 7, 2021June 7, 2021 ሪፖርት
ብዛት ያላቸው ተፈናቃዮች ከግንቦት 16 ቀን 2013 ጀምሮ በጸጥታ ኃይሎች ተይዘዋል
November 24, 2020May 21, 2021 ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በማይካድራ የተፈጸመው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፈጣን ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርት
November 15, 2020May 21, 2021 ጋዜጣዊ መግለጫ
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታና ደኅንነትን ለማጠናከር ፈጣንና የተቀናጀ እርምጃ አስፈላጊ ነው

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup

Signup for the Latest Update from EHRC

    Submit your email here to get the latest update from EHRC.

    Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

    ጠቃሚ ድረ-ገጾች

    • NANHRI
    • GANHRI
    • OHCHR
    • ACHPR

    ተሳተፉ

    • ከእኛ ጋር ለመስራት
    • አግኙን

    ከእኛ ጋር ይገናኙ

    • Facebook
    • Twitter
    • LinkedIn
    • YouTube
    EHRC
    እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶችን የማስተዋወቅ እና
    የማስጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠን ነፃ ብሄራዊ የሰብአዊ መብቶች
    ተቋም ነን
    Submit your email to get the latest update from EHRC

    © 2022 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

    ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎት ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።

    ኩኪዎችን መጠቀም ላይ መስማማትዎን እባክዎ ያሳውቁን።

    Scroll to top
    • የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)
    • ስለ እኛ
      • ስለ ተቋማችን
      • ስለ ባልደረቦቻችን
      • ከእኛ ጋር ለመስራት
      • አግኙን
    • ክልሎች
      • አዲስ አበባ
      • አፋር
      • አማራ
      • ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ
      • ሶማሌ
      • ደቡብ ክልል
      • ኦሮሚያ
    • የስራ ዘርፎች
      • የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ መብቶች
      • የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች
      • የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች
      • የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን መብቶች
      • የሴቶች እና ሕጻናት መብቶች
      • የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ
      • የሰብአዊ መብቶች ትምህርት
    • ጋዜጣዊ መግለጫ
    • ሪፖርት
    • ሚዲያ
      • ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
      • የኢሰመኮ ቪዲዮዎች
      • የኢሰመኮ ጽሑፎች
    • ተጨማሪ መረጃዎች
    • አማርኛአማርኛ
    • EnglishEnglish
    Facebook Twitter
    Search
    Powered by  GDPR Cookie Compliance
    Privacy Overview

    This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

    Strictly Necessary Cookies

    Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

    If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.