Skip to content
Facebook Twitter
  • አማርኛአማርኛ
  • EnglishEnglish
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • ስለ እኛ
    • ስለ ተቋማችን
    • ስለ ባልደረቦቻችን
    • ከእኛ ጋር ለመስራት
    • አግኙን
  • ክልሎች
        • ክልሎች

          ኢሰመኮ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ማስከበርና መጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው ራሱን የቻለ የፌዴራል ተቋም ነው።

        • አዲስ አበባ
        • አፋር
        • አማራ
        • ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ
        • ኦሮሚያ
        • ደቡብ ክልል
        • ሶማሌ
  • የስራ ዘርፎች
        • የስራ ዘርፎች

          እኛ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን የማስፋፋት እና የማስጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠን ገለልተኛ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም ነን
        • የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ መብቶች
        • የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች
        • የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች
        • የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን መብቶች
        • የሰብአዊ መብቶች ትምህርት
        • የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ
        • የሴቶች እና ሕጻናት መብቶች
  • ጋዜጣዊ መግለጫ
  • ሪፖርት
  • ሚዲያ
    • ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
    • የኢሰመኮ ቪዲዮዎች
    • የኢሰመኮ ጽሑፎች
  • ተጨማሪ መረጃዎች
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ኦሮሚያ ክልል፡ የዋስትና መብትን በተቀላጠፈ መንገድ ስለማረጋገጥ

November 16, 2020May 21, 2021 ጋዜጣዊ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበታ ልዩ ችሎት ለአራት ወራት ያህል በእስር በቆዩት በአቶ ለሚ ቤኛ እና…

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበታ ልዩ ችሎት ለአራት ወራት ያህል በእስር በቆዩት በአቶ ለሚ ቤኛ እና በአቶ ዳዊት አብደታ ጉዳይ የዋስትና መብታቸውን በማረጋገጥ የሰጠውን ትክክለኛ ውሳኔ እውቅና ሰጠ፡፡ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ሥራ አስፈጻሚና የፍትሕ አካላት በተመሳሳይ መልኩ የሌሎችንም ተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት መከበሩን እንዲያረጋግጡ ጥሪ ያቀርባል።

ኢሰመኮ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በፍርድ ቤት የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸውና የዋስትና ሁኔታውን አሟልተው ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሰጠላቸው ሰዎች በእስር እንዲቆዩ መደረጉ ፍትሕን የሚያጓድልና ሰብአዊ መብቶችን የሚጥስ ተግባር መሆኑን ጠቅሶ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ማሳሰቡ ይታወሳል።

በዚሁ መሰረት ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች በእስር ስለሚገኙ ሰዎች ሁኔታ ሊወሰድ የሚገባውን እርምጃ ለሚመለከታቸው የክልሉ ኃላፊዎች በማሳወቅ ክትትሉን የቀጠለ ሲሆን፤ በተለያዩ ቦታዎች አበረታች አርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑ ቢታወቅም አሁንም ድረስ በተለይ የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው በእስር የሚገኙ ሰዎች እንዳሉ በተደረጉ ክትትሎች ለማወቅ ተችሏል። ከነዚህ መካከል የአቶ ልደቱ አያሌው እና የዶ/ር ሁሴን ከድር ጉዳይ አፋጣኝ እልባት የሚሻ መሆኑን ኮሚሽኑ አሁንም በጥብቅ ያሳስባል።

ከሐምሌ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ በእስር ላይ ለሚገኙት አቶ ልደቱ አያሌው ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ትዕዛዝ ቢሰጥም፣ ውሳኔው ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቶ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፤ አሁንም በድጋሚ ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ መሰጠቱ ይታወቃል። በኢሰመኮ ምርመራ መሰረት በአቶ ልደቱ ላይ የቀረቡት ክሶች የዋስትና መብት የማያስከለክሉ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ የጤንነታቸው ሁኔታ ማስረጃዎች የዋስትና መብት ጥያቄውን በአፋጣኝ ተግባራዊ ማድረግን አስፈላጊነት ያስረዳል። ስለሆነም የአቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና መብት በአስቸኳይ ሊፈቀድ የሚገባ ነው።

በሌላ በኩል ከሐምሌ 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር ሁሴን ከድር የአጋርፋ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. የዋስትና መብት ፈቅዶላቸዉ ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ከመስጠቱም በተጨማሪ፣ የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ጥቅምት 13ቀን 2013 ዓ.ም. ከፖሊስ በቀረበለት የተጠርጣሪው የምርመራ መዝገብ ላይ በሰጠው ውሳኔ ክስ ለማቅረብ የሚያበቃ ማስረጃ አለማግኘቱን ጠቅሶ የምርመራ መዝገቡን ዘግቷል። ይሁንና ውሳኔው ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቶ ፖሊስ ለኮሚሽኑ እንዳሳወቀው በተጨማሪ ወንጀል በመጠርጠራቸው አሁንም በእስር ላይ ናቸው፡፡ ዶ/ር ሁሴን ከድር አብዛኛውን የእስር ጊዜ የቆዩት በአጋርፋ እስር ቤት ሲሆን፤ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ከተማ ተወስደው አሁንም በኦሮሚያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ኢሰመኮ የተረዳ ቢሆንም፣ ወደ አዲስ አበባ ከመጡ ወዲህ ከቤተሰቦቻቸው አለመገናኘታቸው ኮሚሽኑን አሳስቦታል። ስለሆነም ዶ/ር ሁሴን ከድር በአስቸኳይ በቤተሰባቸው ሊጎበኙ የሚገባ ከመሆኑም በተጨማሪ፤ ሊያስከስስ የሚችል አሳማኝ ክስ ካለ በአፋጣኝ ሊቀርብ፣ አሊያም ከእስር ሊለቀቁ ወይም የዋስትና መብታቸው በአስቸኳይ ሊከበር ይገባል። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እንደገለጹት ‹‹ የዋስትና መብት በሕገ መንግስቱና ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች የተረጋገጠ መሰረታዊ መብት እንደመሆኑ፣ በሕግ በግልጽ ከተመለከቱ ሁኔታዎች በስተቀር የዋስትና መብት በተቀላጠፈ አሰራር ተግባራዊ ሊደረግ የሚገባው ነው። ›› አክለውም “በዚህ ረገድ ፍርድ ቤቶች የተከሳሾችን የዋስትና መብት የሚያረጋግጡ ውሳኔዎችን እየወሰኑ መሆናቸው የሚበረታታ ተግባር ነው” ብለዋል።

Reports & Press Releases

February 12, 2022February 12, 2022 Event Update
Mainstreaming Disability Rights and Rights of Older Persons across all of EHRC’s Departments: a shared responsibility
January 25, 2021June 4, 2021 ጋዜጣዊ መግለጫ
ጋምቤላ ክልል፡ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አፋጣኝ ትኩረት ይሻል
November 14, 2020May 30, 2021 Press Release
The War in Tigray Region and the Worrying State of Human Rights Protection
October 15, 2020May 12, 2021 ሪፖርት
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚወሰዱ እርምጃዎች የሴቶችና ሕፃናትን የጤና መብቶች ታሳቢ ያደረጉ መሆን ይገባቸዋል!

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup

Signup for the Latest Update from EHRC

    Submit your email here to get the latest update from EHRC.

    Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

    ጠቃሚ ድረ-ገጾች

    • NANHRI
    • GANHRI
    • OHCHR
    • ACHPR

    ተሳተፉ

    • ከእኛ ጋር ለመስራት
    • አግኙን

    ከእኛ ጋር ይገናኙ

    • Facebook
    • Twitter
    • LinkedIn
    • YouTube
    EHRC
    እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶችን የማስተዋወቅ እና
    የማስጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠን ነፃ ብሄራዊ የሰብአዊ መብቶች
    ተቋም ነን
    Submit your email to get the latest update from EHRC

    © 2022 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

    ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎት ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።

    ኩኪዎችን መጠቀም ላይ መስማማትዎን እባክዎ ያሳውቁን።

    Scroll to top
    • የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)
    • ስለ እኛ
      • ስለ ተቋማችን
      • ስለ ባልደረቦቻችን
      • ከእኛ ጋር ለመስራት
      • አግኙን
    • ክልሎች
      • አዲስ አበባ
      • አፋር
      • አማራ
      • ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ
      • ሶማሌ
      • ደቡብ ክልል
      • ኦሮሚያ
    • የስራ ዘርፎች
      • የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ መብቶች
      • የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች
      • የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች
      • የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን መብቶች
      • የሴቶች እና ሕጻናት መብቶች
      • የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ
      • የሰብአዊ መብቶች ትምህርት
    • ጋዜጣዊ መግለጫ
    • ሪፖርት
    • ሚዲያ
      • ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
      • የኢሰመኮ ቪዲዮዎች
      • የኢሰመኮ ጽሑፎች
    • ተጨማሪ መረጃዎች
    • አማርኛአማርኛ
    • EnglishEnglish
    Facebook Twitter
    Search
    Powered by  GDPR Cookie Compliance
    Privacy Overview

    This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

    Strictly Necessary Cookies

    Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

    If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.