አረጋውያን በግጭትና በአደጋ ወቅት ጥበቃ የማግኘት ሰብአዊ መብት አላቸው፡፡ (የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የአፍሪካ የአረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል አንቀጽ 14)

ሀገራት፡-  

በተፈጥሮ አደጋዎች፣ በግጭት ሁኔታዎች፣ በእርስ በእርስ ግጭትና በጦርነት ወቅት በሚደረጉ የነፍስ አድን ጥረቶች፣ ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው በሚመለሱበት ወቅት እና በሌሎች የድጋፍ እርምጃዎች ወቅት ለአረጋውያን በቅድሚያ ተደራሽ መሆናቸውን የማረጋገጥ፤

በእድሜ የገፉ ሰዎች በማንኛውም ጊዜ ሰብአዊ የሆነ አያያዝ፣ ጥበቃና ክብር ማግኘታቸውን፤ እንዲሁም አስፈላጊ የሕክምና እርዳታና እንክብካቤ ሳያገኙ እንዳይቀሩ የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፡፡  የአረጋውያንን ጥበቃ የማግኘት መብት እውን ለማድረግ መንግሥታት ሕግ የማውጣት እና ሌሎች አስፈላጊ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው፡፡ (አንቀጽ 2)