ማንኛውም ሰው ክብር ያለው ኑሮ ለመኖር የሚያስችለውን እና በከፍተኛ ደረጃ ሊደረስበት የሚችል አካላዊ እና አዕምሮአዊ ጤንነት የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት (አንቀጽ 41 እና 90)፡-
መንግሥት የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች የማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሃብት ይመድባል
የሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎት፣ የንጹሕ ውሃ፣ የመኖሪያ፣ የምግብና የማኅበራዊ ዋስትና እንዲኖረው ይደረጋል
የጤና መብትን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት
- የጤና ተቋማት/መሰረተ ልማት፣ የጤና ግብዓቶች እና አገልግሎቶች ከአድሎ ነጻ በሆነ መልኩ በተለይም ተጋላጭ ለሆኑ ወይም ለተገለሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ማድረግ
- አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶች አቅርቦትን ማሟላት
- ሁሉም የጤና ተቋማት፣ የጤና ግብዓቶች እና አገልግሎቶች ፍትሐዊ ስርጭት መኖር የሚሉት ከመንግሥት ከሚጠበቁት ዝቅተኛ ዋና ግዴታዎች መካከል ናቸው፡፡
Photo credit: UNICEF Ethiopia/2014/Tsegaye