መንግሥት የሰብዓዊ መብት ጥሰት የምርምራ ውጤት ምክር ሀሳብን ተግባራዊ ለማድረግ ያለው ዝግጁነት አበረታች መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ።
ኢሰመኮ ይህን ያስታወቀው የ10 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 3፤ 2014 ባቀረበበት ወቅት ነው። ኮሚሽኑ “እጅግ አሳሳቢ” ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን የዘረዘረው የፓርላማውን “ልዩ ትኩረት የሚሹ” ጉዳዮች በሚል ባቀረበው የሪፖርቱ ክፍል ነው።
«ምክር ቤቱ አስፈፃሚዉን አካል መከታተል አለበት» አሰመኮ
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፉት 10 ወራት ባከናወናቸው የክትትል እና ምርመራ ስራ የተስተዋሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች “እጅግ አሳሳቢ እየሆኑ” መምጣታቸውን አስታወቀ።
በአፍሪካ ውስጥ እውቅና የተሰጠው ተቋም እንዲሆን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለሕጻናት የሚያደርገው ጥበቃ እና የሚሰጠው የሰብዓዊ መብት ከለላ በአፍሪካ ሰብዓዊ መብት እና ደኅንነት ላይ በሚሰሩ የምሁራን ኮሚቴ መገምገሙን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ምስለ ፍርድ ቤት የተማሪዎች ክርክር ውድድር
ኮሚሽነር መስከረም የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሴቶችን ለመርዳትና ዳግም ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈጸም ለመካላከል የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶች የኢኮሚ፤ የስነልቦናና የጤና ድጋፍ ማድረግ፤ወንጀሉን የፈጽሙትን ተጠያቂ ማደርግና ለፍርድ ማቅረብ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ተመሳሳይ ወንጀል ዳግም እንዳይፈጸም ዋስትና መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።