ከእስር ከተለቀቁት መካከል ሴቶች፣ አረጋውያን፣ የጤና ችግር ያለባቸው እና ሌሎች ጉዳያቸው ተጣርቶ በቀላል ዋስትና የተለቀቁ ሰዎች ይገኙበታል፡፡
በታኅሣሥ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ሁሉም ተባባሪ ድርጅቶች በጋራ ጊዮን ሆቴል በሚገኘው ጋርደን ግሩቭ ዎክ መናፈሻ የጋራ ዝግጅት ላይ የዚህን ዓመት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን መሪ-ቃል ዋና መልዕክት በማስተዋወቅ የዝግጅቶቹን መዝጊያ መርኃ ግብር አዘጋጅተዋል።
ኢሰመኮ ባለፉት ሁለት ዓመታት የማቋቋምያ አዋጁን አሻሽሎ ተዓማኒ እና ውጤታማ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ለመሆን ላደረገው ከፍተኛ ጥረት እውቅና ሰጠ::
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በኅዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዳማ ኦሊያድ ሲኒማ፣ በኅዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ደግሞ በሀዋሳ ከተማ ሌዊ ሲኒማ በመጨረሻም በታኅሣሥ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በጋርደን ግሩቭ ዎክ መናፈሻ ይካሄዳል::
ኮሚሽኑ ይህንኑ ቀን ለማሰብ ባሰራጨው በዚህ አጭር ቪድዮ የአካል ጉዳተኞችን እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመንግስትም ሆነ በሌሎች አካላት ከወዲሁ መወሰድ ስለሚችሉ እርምጃዎች ግንዛቤ ይሰጣል፣ ውትወታ ያደርጋል።
ለባለፉት በርካታ ወራት ሰፊ አካታች ሂደት ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የስትራቴጂ እቅድ ኮሚሽኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊሰሩና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሎ የለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮችንና ዋና ዋና ተግባራትን አካቷል።
ኢሰመኮ በማቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ወቅት ሰብአዊ መብቶችን የሚከታተል መሆኑንና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለኮሚሽኑ የክትትል ተግባራት ትብብር የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ለማስታወስ ይወዳል፡፡