የውድድሩ አላማ ተማሪዎች ስለ ሰብዓዊ መብቶች ፣ ስለ ፍትሕ አስተዳደር እና ዳኝነት እንዲያውቁ እና የመብት ጥሰቶችን እንዲከላከሉ ነው
ከመግለጫው ጋር በተያያዘ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት የኢሰመኮ የሕግና ፖሊሲ ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ታሪኳ ጌታቸው፣ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና ሌሎች የሚዲያ ሰራተኞች ሰብዓዊ መብታቸው ሊጠበቅ እንደሚገባ እና መጠየቅ ያለባቸውም በመገናኛ ብዙኃን ሕግ መሰረት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሀገራዊ ምርጫ 2013 ዓ.ም. ባለ6 ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ይፋ በማድረግና ለሰብአዊ መብቶች ትኩረት እንዲሰጥ ከመወትወት በተጨማሪ፤ በቅድመ ምርጫውና በምርጫው ቀን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሲያከናውን ቆይቷል።
የተራዘመ የቅድመ-ክስ እስራትን እና ተያያዥ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመከላከል የሁሉንም ፍትሕ አስተዳደር አካላት ቁርጠኛ ጥረት ይሻል
ስብሰባው የሚካሄድበት ቀን ከእ.ኤ.አ. 2010 ጀምሮ መጋቢት 15 ቀን የሚታሰበው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ እውነቱን የማወቅ መብት እና የተጎጂዎች ሰብአዊ ክብር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታሰብበት ዕለት ነው
ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን በምናስብበበት በዚህ ወር ውስጥ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ማሻገር በሴቶችና ሕፃናት ላይ ሰብአዊ መብቶች ጥሰት እያደረሰ በመሆኑ ምላሽ ለመስጠት የሚደረጉ ጥረቶችን ውጤታማ ለማድረግ በጋራ መስራት አስፈላጊነትን ማስታወስ ተገቢ ነው
ኮሚሽኑ ዓላማውን ለማስፈጸም ከሚሰራቸው ሰብአዊ መብቶችን የማስተማር እና የማስፋፋት ስራ ውጤታማ እንዲሆን ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በአጋርነት የሚሰራ ሲሆን፣ ከሀገራዊ የኪነጥበብና የሥነ ጥበብ ባለሞያዎችና ማኅበራት ጋር የሚያደርገውን ትብብር በተመሳሳይ መልኩ እኩል ክብደት የሚሰጠው ነው
ያቀረባቸው ምክረ ሃሳቦች እንዲፈጸሙ የጣምራ ምርምር ቡድኑ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል
ለሁለት ቀናት የሚካሄደው የውይይት መድረክ ሲገባደድ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሚናና የስራ ኃላፊነት ተሻሽሎ በወጣው መመሪያ መሰረት በመለየት ሁለተኛውን ውድድር ለማከናውን የወጣውን መርኃ ግብር ለመተግበር የጋራ መግባባት ላይ የሚደርሱበት እንደሚሆን ይጠበቃል
ከእስር ከተለቀቁት መካከል ሴቶች፣ አረጋውያን፣ የጤና ችግር ያለባቸው እና ሌሎች ጉዳያቸው ተጣርቶ በቀላል ዋስትና የተለቀቁ ሰዎች ይገኙበታል፡፡