አማራ፣ ኦሮሚያ፦ መንግሥት በተስፋፋ ሁኔታ የሚፈጸም የሰዎች እገታን ሊያስቆምና ተጠያቂነትንም ሊያረጋግጥ ይገባል

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አሳሳቢ ሆኖ የቀጠለውን የእገታ ተግባር ዘላቂ በሆነ መልኩ ለማስቆም ለሰዎች እገታ መነሻና አባባሽ ምክንያት የሆነውን የሰላም መደፍረስና የትጥቅ ግጭትን በዘላቂነት በሰላማዊ መንገድ መፍታትን ጨምሮ ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ነው