የሴቶች የእኩልነት መብት

አባል ሀገራት በሁሉም መስክ በተለይም በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ መስኮች የሴቶችን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥና ከፍ ለማድረግ እንዲሁም ሴቶች ከወንዶች እኩል በሰብአዊ መብቶቻቸው እና መሠረታዊ ነጻነቶቻቸው መጠቀም እንዲችሉ ሕግ ማውጣትን ጨምሮ አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች ሁሉ መውሰድ አለባቸው