የአረጋውያን እንክብካቤና ድጋፍ የማግኘት መብት

አረጋውያን በማንኛውም መጠለያ፣ መንከባከቢያ ወይም የድጋፍ ማእከል ውስጥ በሚኖሩበት ጊዜ ሰብአዊ መብቶቻቸው እና መሠረታዊ ነጻነቶቻቸው ሊረጋገጡላቸው ይገባል፤ይህም ስለሚደረግላቸው እንክብካቤ እና ስለሕይወታቸው ሁኔታ የመወሰን መብታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን፣ እምነታቸውን፣ ፍላጎቶቻቸውን እና ግላዊ ሕይወታቸውን ሙሉ በሙሉ ማክበርን ይጨምራል።