የአካል ጉዳተኛ ሴቶች ጥበቃ

አባል ሀገራት አካል ጉዳተኛ ሴቶችና ሴት ልጆች ለተደራራቢ አድልዎ የተዳረጉ መሆናቸውን ዕውቅና ይሰጣሉ፤ ይህንንም ከግንዛቤ በማስገባት በሁሉም ሰብአዊ መብቶችና መሠረታዊ ነጻነቶች ሙሉ እና እኩል ተጠቃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እርምጃዎችን ይወስዳሉ