የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሀገራዊ ምርጫ 2013 ዓ.ም. ባለ6 ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ይፋ በማድረግና ለሰብአዊ መብቶች ትኩረት እንዲሰጥ ከመወትወት በተጨማሪ፤ በቅድመ ምርጫውና በምርጫው ቀን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሲያከናውን ቆይቷል።
ኢትዮጵያ በ2012 ዓ.ም. የአፍሪካ ሕብረት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃና ድጋፍ ስምምነት (የካምፓላ ስምምነት) መቀበሏን ተከትሎ በወጣው ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር 1187/2020 እንደተመለከተው፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ማለት “በጦርነት፣ በመጠነ ሰፊ ብጥብጦች፣ በሰብአዊ መብት ጥሰቶች ወይም ሰው ሠራሽ ወይም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ወይም በሚያስከትሏቸው ውጤቶች የተነሳ ከሚኖሩባቸው ቤቶች ወይም መደበኛ የመኖሪያ ቦታዎች እንዲሸሹ ወይም ለቅቀው እንዲወጡ የተገደዱ ነገር...