
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ ዛሬ አመሻሹን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ባለፈው ሳምንት ከማክሰኞ ጀምሮ እስከ ሃሙስ ቀጥሎ ነበር ባለው ንጹሃን ዜጎች ላይ ባነጣጠረው የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማው የታጣቂዎች ጥቃት፤ ቢያንስ ከ60 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ሲገደሉ ከ70 በላይ ከከባድ እስከ ቀላል የመቁሰል አደጋን አስተናግደዋል፡፡ እንደ ኮሚሽኑ መግለጫ ከ20 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ ወደ ወረዳው ከተማ ኦቦራ ተፈናቅለዋል