Annual Ethiopia Human Rights Situation Report (June 2024 – June 2025)
ከሰኔ 2016 እስከ ሰኔ 2017
የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት
ተዛማጅ ሰነዶች
ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነውና ለአራተኛ በጀት ዓመት በዚህ መልኩ ተጠናቅሮ ይፋ የተደረገው ይህ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዓመታዊ ሪፖርት ኮሚሽኑ ባደራጃቸው ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች እና የከተማ ጽሕፈት ቤቶች አማካኝነት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ጠቅለል ባለ መልኩ የሚዳስስ ነው።
“በሪፖርቱ በተሸፈነው ጊዜ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ በርካታ አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች ለመከሰታቸው እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋና ምክንያት የሆነውን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ የትጥቅ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረሶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት ብቸኛው አማራጭ ነው።”
Human rights overview (2024 – 2025)