ኢሰመኮ ይህን ያለው ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በ4 ክልሎች የተካሄደውን የ6ኛ ዙር ቀሪና ድጋሚ ምርጫ የሰብአዊ መብቶችን ክትትል በመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ነው
ሰኔ 21፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሰኔ 16 ቀን በተካሄደው የ6ኛው የቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ወቅት የነበሩ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ክትትል የያዘ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ አድርጓል
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዕለቱ ምርጫ እንዳይካሄድ ከወሰነባቸው አካባቢዎች በስተቀር ምርጫው በአብዛኛው ሰላማዊ እና የሰብአዊ መብቶች መርሖችን ባከበረ መልኩ ተጠናቋል
በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግርዛትና ተደጋጋሚ ግርዛትን ለማስቆም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማኅበረሰቡን ለማስተማርና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጋራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል
በጤናና በትምህርት፣ እንዲሁም በሌሎችም ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪ የመንግሥት ተቋማት ላይ ቅኝት በማድረግ ምርመራ ማድረጉን የኮሚሽኑ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሥራ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ብራይትማን ገብረሚካኤል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጉራጌ ዞን እና በቀቤና ልዩ ወረዳ መካከል የነበረውን አለመግባባት ተከትሎ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የተከሰተውን የጸጥታ መደፍረስና ያስከተለውን ጉዳት ከአካባቢው ነዋሪዎች በቀረበለት አቤቱታ መነሻነት ከጥቅምት 20 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በቦታው በመገኘት ጭምር ምርመራ ማከናወኑን አስታውቋል
በወልቂጤ ከተማ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተከሰተው ሁከት እና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ እንዲሁም ለተፈናቃዮች እና ተጎጂዎች አስፈላጊው ድጋፍ እና ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል
በአዲስ መልክ በተደራጀው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃዲያ ዞን ለሚገኙ መምህራን “ተገቢው ደመወዝ በወቅቱ ባለመከፈሉ ምክንያት” የመንግስት ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን እና 100 ሺህ ገደማ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
በአዲስ መልኩ በሚዋቀሩ አካባቢዎች የሚነሱ የደመወዝ እና ተያያዥ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት በጤና እና በትምህርት መብት እንዲሁም በአካባቢዎቹ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሉ ሥጋቶችን ይቀርፋል
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመዋቅር እና የአስተዳደር ጥያቄዎች ለሰላም እጦት ምክንያት መሆናቸው እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዐስታወቀ ፡፡ በክልሉ በጉራጌ ዞን እና በቀቤና ልዩ ወረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት በአካባቢው የፀጥታ መደፍረስን ማስከተሉን ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው የምርመራ ሪፖርቱ ዐስታውቋል