የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 26
- ማንኛውም ሰው የግል ሕይወቱ፣ ግላዊነቱ፣ የመከበር መብት አለው። ይህ መብት መኖሪያ ቤቱ፣ ሰውነቱና ንብረቱ ከመመርመር እንዲሁም በግል ይዞታው ያለ ንብረት ከመያዝ የመጠበቅ መብትን ያካትታል።
- የመንግሥት ባለሥልጣናት እነዚህን መብቶች የማክበርና የማስከበር ግዴታ አለባቸው። አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲፈጠሩና ብሔራዊ ደኅንነትን ወይም የሕዝብን ሰላም ለማስጠበቅ፣ ወንጀልን ለመከላከል፣ ጤናንና የሕዝብን ሞራል ለመጠበቅ ወይም የሌሎችን መብትና ነጻነት የማስከበር ዓላማዎች ላይ በተመሠረቱ ዝርዝር ሕጎች መሠረት ካልሆነ በስተቀር የእነዚህ መብቶች አጠቃቀም ሊገደብ አይችልም።