ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት አንቀጽ 6 (1) እና (2)  

  • አባል ሀገራት አካል ጉዳተኛ ሴቶችና ሴት ልጆች ለተደራራቢ አድልዎ የተዳረጉ መሆናቸውን ዕውቅና ይሰጣሉ፤ ይህንንም ከግንዛቤ በማስገባት በሁሉም ሰብአዊ መብቶችና መሠረታዊ ነጻነቶች ሙሉ እና እኩል ተጠቃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። 
  • አካል ጉዳተኛ ሴቶች በዚህ ስምምነት በተደነገጉት ሰብአዊ መብቶችና መሠረታዊ ነጻነቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣ አባል ሀገራት የሴቶችን የተሟላ ልማትና ዕድገት ዕውን ለማድረግ እና ለማብቃት የሚያስችሉ ተገቢ እርምጃዎችን ሁሉ ይወስዳሉ።