ማንኛውም ሰው የማሰብ፣ የኅሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው
Everyone has the right to freedom of thought, conscience and religion
ማንኛውም ሰው የትምህርት መብት አለው
Everyone has the right to education
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሠረተ ልዩነት ሳይደረግበት በማናቸውም የመንግሥት ደረጃ በየጊዜው በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥ እና የመመረጥ መብት አለው
Every Ethiopian national, without any discrimination based on colour, race, nation, nationality, sex, language, religion, political or other opinion or other status, has the right to vote and to be elected at periodic elections to any office at any level of government
አባል ሀገራት ለአካል ጉዳተኞች የፖለቲካ መብቶችን እና በእነዚህ መብቶች ከሌሎች ጋር በእኩልነት የመጠቀም ዕድልን ያረጋግጣሉ። እንዲሁም የመምረጥና የመመረጥ መብትና ዕድልን ጨምሮ አካል ጉዳተኞች በቀጥታ ወይም በነጻነት በተመረጡ ተወካዮች አማካኝነት በፖለቲካና በሕዝባዊ ሕይወት ውስጥ ከሌሎች ጋር በእኩልነት ውጤታማ እና የተሟላ ተሳትፎ ማድረግ መቻላቸውን ያረጋግጣሉ
States Parties shall guarantee to persons with disabilities political rights and the opportunity to enjoy them on an equal basis with others, and shall undertake to ensure that persons with disabilities can effectively and fully participate in political and public life on an equal basis with others
ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው
Everyone has the right to bring a justiciable matter to, and to obtain a decision or judgement by, a court of law or any other competent body with judicial power