ኢሰመኮ ከአፍሪካ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ትስስር እና ከአባል ተቋማቱ ጋር በመተባበር 16ኛውን ዓመታዊ እና ጠቅላላ ጉባኤ በስኬት ለማስተናገድ ዝግጁ እና ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል
በሰብአዊ መብቶች ተኮር አሠራር፣ በሽግግር ፍትሕ፣ በአረጋውያን መብቶች እና በተጠርጣሪዎች መብቶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሰጥተዋል
በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ችግሩን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እና ልዩነቶችን በሕግ መሠረት በምክክርና በመግባባት ለመፍታት እንዲሠሩ ኢሰመኮ ያሳስባል
ኢሰመኮ ከፌዴራል እና ከክልል መንግሥታት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ያደረጋቸው ተከታታይ ውይይቶች የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን በማጠናከር እና ጥሰቶችን በመከላከል ረገድ አበረታች ውጤቶችን አስገኝተዋል
በክልሉ ያለውን የታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን ለማሻሻል በትኩረትና በቅንጅት መሥራት ያስፈልጋል
በአርብቶ አደር አካባቢዎች ትምህርት የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት እና በቅንጅት ሊሠሩ ይገባል
የዚህ ዓመት ውድድር “የመማር መብት በትጥቅ ግጭት ዐውድ ውስጥ” (The Right to Education in Situation of Armed Conflict) በሚል ምናባዊ ጉዳይ ላይ ያተኩራል
የስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች መብቶች ጥበቃ በሀገራዊ እና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ማዕቀፎች መሠረት እንዲተገበር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ትብብር ሊያደርጉ ይገባል
በቂ የመኖሪያ ቤት የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራት ከሰብአዊ መብቶች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል