Photo by: Ollivier Girard/CIFOR

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተለይም በሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ እንዲነሳ መወሰኑን ኮሚሽኑ በበጎ ተመልክቷል:: ኮሚሽኑ በአስቸኳይ ሁኔታ ወቅት ከአዋጁ አተገባበር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር የዋሉ እና አሁንም ያልተለቀቁ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ በድጋሚ ያሳስባል።

በተጨማሪም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ስር ውለው የተለቀቁ ሰዎችም በእስር ስለመቆየታቸው ማረጋገጫ ባለማግኘታቸው ወደ ስራ መመለስ አለመቻልን ጨምሮ ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውን ባደረገው ክትትል ተገንዝቧል፡፡ ስለሆነም ሰዎች በእስር የቆዩበትን ጊዜ ማስረጃና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች የመስጠቱን ሂደት እንዲፋጠንና ሰዎች ወደ መደበኛ ሕይወታቸው መመለስ እንዲችሉ እንዲደረግ ኢሰመኮ ያሳስባል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የታሰሩ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል