የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ለሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት አሳሳቢና መሻሻል የሚሏቸውን ጉዳዮች አስቀምጠዋል፡፡
በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግሥት ኃይሎች መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም አልፎ አልፎም ግጭቶች ሪፖርት መደረጋቸው እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።
በሶማሌ ክልል ቦምባስ ከተማ በባህላዊ ሥነ ሥርዓት የጎሳ መሪ ለመምረጥ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በፀጥታ ኃይሎችና በታጠቁ ግለሰቦች በተፈጸሙ ጥቃቶች የ11 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮነነ።
ቋሚ ኮሚቴው የኮሚሽኑን የአሥር ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባዳመጠበት ወቅት፤ ኮሚሽኑ በሀገር ውስጥ ላሉ የዴሞክራሲ ተቋማት እና ለሌሎች ሀገራት ጭምር ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን እንደተረዳ ገልጿል፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት መክንያት በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በምርመራ በመለየት መደረግ ያለባቸውን አስፈላጊ ነገሮች እንዲደረጉ ለማመላከትና ለማመቻቸት ነው።
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ዝቅተኛ ደመወዝ የሚወስነውን ቦርድ የሚያቋቁም ደንብ እንዲያወጣ ለመንግሥት ጥሪ አቀረበ።
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኢንተርኔት እየተዘዋወረ ያለውን የመንግሥት ወታደሮች አንድ የትግራይ ተወላጅ ወንድ ልጅ ሲያንገላቱ ከዚያም በጥይት ሲመቱ የሚያሳይ የሚመስል የቪድዮ ምስል በመመርመር ላይ መሆኑን አስታውቋል።