የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል ለሚባሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች ነጻ የሕግ ድጋፍ፣ የመጠለያ፣ የጤና፣ የማኅበራዊና የሥነልቦናዊ አገልግሎት በመስጠት የሰብአዊ አገልግሎቱን የተሟላ ለማድረግ ያስችላል
በክልሉ ከሚስተዋሉ ፈታኝ ሁኔታዎች አንፃር የሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች አበረታች ቢሆኑም ሴት ተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች የሚያዙበት ቦታ አለመለየትና ቅድሚያ አለመስጠት ለተጨማሪ የመብቶች ጥሰት ያጋልጣቸዋል
ማረሚያ ቤቶቹን በሚፈለገው ልክ ለማሻሻል የበጀት እጥረት ያለባቸው መሆኑን፤ በኢሰመኮ የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝት እንደሚሠሩ በማረጋገጥ በዚህ ረገድ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል
EHRC reiterates its readiness to cooperate with the ICHREE within the framework of cooperation proposed, including support to the ICHREE on discussions with the State to grant access to affected areas in Northern Ethiopia
ኢሰመኮ መንግስት ስላልተባበረው በአዋሽ ሰባት ያሉትን ተፈናቃዮች መጎብኘት እንዳልቻለ ገልጿል
በአፋር ክልል መንግሥት በሰመራና አጋቲና የተባሉ ሁለት መጠለያዎች ውስጥ ለደኅንነታቸው በሚል ተይዘው ከቆዩ ዘጠኝ ሺህ አሥር ያህል የትግራይ ተወላጆች የሰመራዎቹ ሙሉ በሙሉ ወደ ቀደመ ቀያቸው አብአላ ከተማ መመለሳቸው የሚያስመሰግን ተግባር መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ
በሰመራ ጣቢያዎች ተይዘው የነበሩ ሰዎች በኢሰመኮ ምክረ ሃሳቦች መሰረት እንዲለቀቁና በፍላጎታቸው መሰረት ወደመጡባቸው አካባቢዎች እንዲመለሱ መደረጉ ኢሰመኮ በበጎ የሚመለከተው ነው
‹‹የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን ግጭትን በሚቀንስ መንገድ ቢሆን ዓመቱ በጣም ሰላማዊ ይሆናል›› ራኬብ መሰለ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር
ሰዎቹ ከሌሎች የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች በተለየ መልኩ ከሕግ አግባብ ውጪ እና የመንቀሳቀስ መብታቸው ተነፍጎ፣ የሰብአዊ ድጋፍ በበቂ ሁኔታ ሳይቀርብላቸው በጃሬ መጠለያ ጣቢያ ለበርካታ ወራት ተይዘው ቆይተዋል
ኢሰመኮ በካምፖቹ የነበሩ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመር እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በበጎ የሚቀበለው ነው