በክልሉ መንግሥት የተጀመሩ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሥራዎች እንዲቀጥሉ እና በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ ሊደረግ እንደሚገባ ኮሚሽኑ በሪፖርቱ አሳስቧል
የተሟላ ፍትሕ የሚረጋገጠው ጥፋተኞች ተጠያቂ ሲሆኑ፣ የተበደሉ ሲካሱና ለወደፊትም ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት አስፈላጊ እርምጃዎች ተግባራዊ ሲደረጉ ስለሆነ ለዚህ ውጤት በቁርጠኝነት መሥራት መቀጠል አለበት
በሪፖርቱ እንደተመለከተው ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም በኢታንግ ልዩ ወረዳ ሥር በሚገኝ ፒኝዋ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አንድ ግለሰብ መጥፋታቸውን ተከትሎ፣ በፒኝዋ ቀበሌ እና አጎራባች በሆነው በሌር ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት በወቅቱ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የግለሰቦች እና የተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት እና ዘረፋ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል
EHRC’s latest report details the human rights violations that occurred in several districts of the region, including Itang Special District, Gambella District, Gog District, and the region’s capital, Gambella City
በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ወረዳዎች ከግንቦት 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተከሰቱ ግጭቶች ቢያንስ የ138 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና 113 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ማረጋገጥ መቻሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ አስታወቀ
ኮሚሽኑ ከመስከረም 20 እስከ መስከረም 30/ 2016 ዓ.ም ድረስ አከናውኘዋለሁ ባለው ምርመራ ግጭቶቹ በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላና ጉግ ወረዳዎች እንዲሁም በክልሉ ዋና ከተማ ጋምቤላ ተከስተዋል ብሏል
በጋምቤላ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በተካሄዱ ግጭቶች፤ ቢያንስ 138 ሰዎች መገደላቸውን እና በ113 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በግጭቶቹ የተነሳ በርካታ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን፣ መኖሪያ ቤቶች እና ንብረቶች መቃጠላቸውን እንዲሁም ዘረፋ መፈጸሙን ኮሚሽኑ ገልጿል
የጥፋተኞችን ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የማኅበረሰብ ውይይቶች፣ የሰላምና ዕርቅ ተጨባጭ እርምጃዎች ለዘላቂ መፍትሔ አስፈላጊ ናቸው
በጋምቤላ ክልል የቤተሰብ ሕግ አፈጻጸም የታዩ ክፍተቶችን በሚገባ ለመመለስ ሕጉ የማኅበረሰቡን ወግ፣ ባህል፣ እሴቶች እና የአኗኗር ዘይቤ እንዲሁም ኅብረተሰቡ አሁን ያለበትን የእድገት ደረጃ ያማከለ ሆኖ መሻሻል ያስፈልገዋል
በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች የሚያስፈልጓቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት እንቅፋት የሆኑ ችግሮች መኖራቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ