በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ የተጀመረው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል ለሦስተኛ ጊዜ ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ይካሄዳል።

የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ ለማዳበር ሰፊ ተደራሽነት ያለውን የፊልም ጥበብን በመጠቀም በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ፊልሞች ለእይታ እና ለውይይት ይቀርባሉ።

በፌስቲቫሉ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው በፊልም እና በሌሎች የኪነጥበብ ዘርፍ ሙያ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች፣ በሰብአዊ መብቶች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የሚሠሩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኀን፣ ተማሪዎች እና ሌሎች ተመልካቾች ይታደሙበታል፡፡