በምእራብ ወለጋ በትላንትናው እለት በነዋሪዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት በአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ አለመሻሻሉንና ይልቁንም በክልሉና በአዋሳኝ አካባቢዎች እየተስፋፋና ተያያዥ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እያስከተለ መሄዱን ያሳያል::

የፌዴራል መንግስት አካባቢውን ለማረጋጋት በጊዜያዊነት ከሚወስዳቸው እርምጃዎች በተጨማሪ ነዋሪዎች በየትኛውም ክልል በሰላም የመኖር መብታቸውን በሚያረጋግጥ መልኩ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር መጠነ ሰፊና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ እቅድ መንደፍ ይኖርበታል::