Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

አዳዲስ አስተዳደር እና መዋቅር በሚዘረጉባቸው አካባቢዎች ከበጀት እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች እና የሰብአዊ መብቶች እንድምታ

December 23, 2023August 28, 2024 Press Release

በአዲስ መልኩ በሚዋቀሩ አካባቢዎች የሚነሱ የደመወዝ እና ተያያዥ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት በጤና እና በትምህርት መብት እንዲሁም በአካባቢዎቹ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሉ ሥጋቶችን ይቀርፋል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Download Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለይም አዲሱ የክልል አደረጃጀት ተከትሎ የተለያዩ አስተዳደሮች እና መዋቅሮች መልሶ መቋቋም ወይም ተያያዥ ውሳኔዎች ሂደት ጋር የሚነሱ የደመወዝ መዘግየት እና ያለመከፈል የተመለከቱ አቤቱታዎችን፣ እንዲሁም ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል። በተለይም ከጥቅምት 21 ቀን እስከ ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በሾኔ ከተማ አስተዳደር፣ ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ፣ ምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ፣ ሆሳዕና ከተማ አስተዳደር እና በጎምቦራ ወረዳ በመገኘት፣ ተጎጂ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ የመንግሥት አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን እና የሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎችን በማነጋገር እንዲሁም የጤና እና የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የመስክ ምልከታ በማድረግ መረጃ እና ማስረጃ በማሰባሰብ ምርመራ አድርጓል።

ለምሳሌ በሃዲያ ዞን ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው የመንግሥት ሠራተኞች እንደሚያስረዱት ከደመወዝ ጋር የተያያዙ ችግሮች ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ የሚስተዋል ሲሆን፣ ከችግሮቹ መካከልም በየወሩ መጨረሻ ሊከፈል የሚገባው ደመወዝ ከ10 እስከ 20 ቀን እንደሚዘገይ እና በተለያዩ ወቅቶች መከፈል ከነበረበት ሙሉ ደመወዝ 30፣ 50 እና 70 በመቶው ብቻ ሲሰጥ መቆየቱን የሚያጠቃልል ነው። ችግሩ ተባብሶ በዋናነት ከፖሊስ፣ ፍርድ ቤቶች እና ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በስተቀር በአብዛኛው የመንግሥት ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ደመወዝ ከነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ምርመራው እስከተከናወነበት ጊዜ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ በመቆየቱ ለዘርፈ ብዙ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ መዳረጋቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ኅብረተሰቡ የጤና እና የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አገልግሎት በማቆማቸው ወይም በሙሉ ዐቅም አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው ሕክምና ለማግኘት ወደ አጎራባች ዞኖች ለመሄድ በመገደዳቸው ለእንግልትና ለሕይወት አደጋ ተጋልጠናል ብለዋል። በከተማ አስተዳደሩ እና በወረዳዎቹ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች እስከ ኮሚሽኑ ምርመራ ወቅት ድረስ (ጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም.) ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የከተማና ወረዳ አስተዳደር ኃላፊዎች በበኩላቸው ችግሩ መኖሩን ገልጸው ከምክንያቶች መካከል የውስጥ (የአካባቢ) ገቢ ማነስ አንዱ መሆኑን አስረድተዋል። ለሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ የሚውል ገንዘብ የሚገኘው ከፌዴራል መንግሥት ተመድቦ በዞን በኩል የሚመጣ በጀት እና የከተማና የወረዳ አስተዳደሮች ከአካባቢው የሚሰበስቡት ገቢ ተደምሮ እንደሆነና አስተዳደሮቹ ይህን ከውስጥ (ከአካባቢው) መሰብሰብ የሚጠበቅባቸውን ገቢ ለማሟላት ዐቅም ስለሌላቸው ለበጀት እጥረቱ አንዱ መንስዔ እንደሆነ ገልጸዋል። ከፌዴራል መንግሥት ተመድቦ የሚመጣው በጀት በአንዳንድ ምክንያቶች ለሌሎች ጉዳዮች መዋሉም (ለምሳሌ ለማዳበሪያ ግዢ) ሌላ ምክንያት እንደሆነ ኃላፊዎች ያስረዳሉ።

በኃላፊዎቹ የተነሳው ሌላው ምክንያት የሠራተኞች ቅጥር ሲሆን፣ በተለያዩ ወቅቶች የተፈጸሙ እና ያልተጠኑ የሠራተኞች ቅጥሮች መኖራቸውንና ይህንንም በተገቢው መንገድ ለማጥራት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል። 

የሃዲያ ዞን አስተዳደር ኃላፊዎች በበኩላቸው ችግሩ በዞኑ ውስጥ ካሉ 19 መዋቅሮች ውስጥ በስምንቱ (ሾኔ ከተማ አስተዳደር፣ ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ፣ ምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ፣ ሲራሮ ባድዋቾ ወረዳ፣ ጎምቦራ ወረዳ፣ ጊቤ ወረዳ፣ ዱና ወረዳ እና ምዕራብ ሶሮ ወረዳ) መኖሩን ገልጸው፣ ምንም እንኳን የጥሬ ገንዘብ እጥረት በመኖሩ እንዲሁም የግብአት ዕዳ ተቀንሶ ከክልል ለዞኑ የሚላከው በጀት ከሚያስፈልገው መጠን ያነሰ ቢሆንም ጉድለቱን በብድር በማሟላት ለከተማና ወረዳ አስተዳደሮች ለደመወዝ ክፍያ የሚያስፈልገውን ሙሉ የገንዘብ መጠን ሲልኩ መቆየታቸውን ይገልጻሉ። ይህ ሆኖ ሳለ ከከተማና ወረዳ አስተዳደር ሠራተኞች የሚነሳው የደመወዝ ክፍያ ችግር ትክክለኛ ምክንያት ምን እንደሆነ ለማጣራት አምስት የክትትል ቡድን ተደራጅቶ በ19ኙም የከተማ እና ወረዳ አስተዳደሮች ከጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ መሰማራታቸውን እና ቡድኑ በሚያቀርበው ግኝት መሠረት ዞኑ የማስተካከያ እርምጃዎችን የሚወስድ መሆኑን ገልጸዋል።

የከተማና ወረዳ አስተዳደሮቹ ይህ አሠራር መኖሩን አረጋግጠው ነገር ግን ከሚላከው ገንዘብ ወደ ኋላ የነበሩ እዳዎች ስለሚከፈሉ ችግሩ መቀጠሉን አስረድተዋል።

የሥራ መብት በተለያዩ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች ዕውቅና ካገኙ መሠረታዊ ሰብአዊ መብቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የሠራተኞች ተገቢውን ክፍያ በሙሉ እና በወቅቱ የማግኘት መብትን የሚያጠቃልል ነው። ለሠራተኞች ተገቢውን ደመወዝ እና ሌሎች ክፍያዎችን በወቅቱ አለመክፈል ሠራተኞች እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ማስተዳደር የሚችሉበትን መንገድ የሚገድብ እና የሥራ መብት ጥሰት ሆኖ የሚቆጠር ነው። ይህን ሁኔታ በመገንዘብ የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) በደመወዝ ጥበቃ ስምምነት 1949 (ቁጥር 95) አንቀጽ 12 እና በደመወዝ ጥበቃ ምክረ ሐሳብ 1949 (ቁጥር 85) አንቀጽ 4 ሥር የደመወዝ ክፍያ በመደበኛነት ሊከፈል እንደሚገባና በተለይም ደመወዛቸው በየወሩ ወይም በዓመት ተወስኖ ለተቀጠሩ ሠራተኞች ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ የደመወዝ ክፍያ ሊፈጸም እንደሚገባ ይደነግጋሉ።

ይህ መብት በሀገራዊ ሕጎች ዕውቅና ያገኘ እና በፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2017 እና በደቡብ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 175/2011 ጭምርም የተደነገገ ነው። ተገቢውን ደመወዝ በወቅቱ አለመክፈል የሥራ መብት ጥሰት ከመሆኑም በተጨማሪ ሌሎች በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚያዊ፣ የማኅበራዊ እና የባህላዊ መብቶች ቃልኪዳን ውስጥ ጥበቃ ያገኙ መብቶች ጥሰትን የሚያስከትል ነው።

የጤና መብት ጋር በተያያዘ ምልከታ በተደረገባቸው የከተማና ወረዳ አስተዳደሮች ውስጥ የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ ለማረጋገጥ ተችሏል። ለአብነትም በሾኔ ከተማ ከ60 ሺህ ሰው በላይ ይገለገልባቸው የነበሩ አንድ ጤና ጣቢያ እና አራት ጤና ኬላዎች፣ በምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ ከ 144 ሺህ ሰው በላይ የሚገለገልባቸው ስድስት ጤና ጣቢያዎች እና 27 ጤና ኬላዎች እንዲሁም በምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ ከ120 ሺህ ሰው በላይ የሚገለገልባቸው አራት ጤና ጣቢያዎች እና 22 ጤና ኬላዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት በተለይም በግል የጤና ተቋማት ለመታከም ዐቅም የሌላቸውና ከዚህ በፊት በማኅበረሰብ ጤና መድኅን ሽፋን በነዚህ ተቋማት አገልግሎት ሲያገኙ የቆዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በከፋ የጤና ችግር ውስጥ ይገኛሉ። በተጨማሪ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከጥቅምት 5 እሰከ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት አቋርጦ የነበረ መሆኑንና የነሐሴ ወር ደመወዝ በጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. 84% ብቻ ተከፍሎ ሥራ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል። ሆስፒታሉ ሥራ አቋርጦ የነበረው ሠራተኞቹ ከደመወዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ የሥራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው ነበር። የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ650 ሺህ በላይ ለሚሆን ሰዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ፣ ምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ፣ ሲራሮ ባድዋቾ ወረዳ፣ ሾኔ ከተማ እንዲሁም ከአጎራባች ወላይታ ዞን ዳመወት ፉላሳ እና ምዕራብ አርሲን የሚያገለግል ነው።

የመማር መብትን አስመልክቶ ምርመራው ባካለላቸው የሾኔ ከተማ አስተዳደር፣ ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ፣ ምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ እና ጎምቦራ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት በመስከረም 14 ቀን የ2016 ዓ.ም መጀመር የነበረበት ትምህርት ምርመራው እሰከ ተደረገበት ጊዜ ድረስ እንዳልተጀመረ ለማረጋገጥ ተችሏል። ምንም እንኳን ለትምህርት ዘመኑ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች (የተማሪዎች ምዝገባ፣ ተማሪዎችን በየክፍሉ መደልደል እና ለመምህራን ክፍለ ጊዜ የመሸንሸን ተግባራት) የተሠሩ ቢሆንም ለመምህራኑ ተገቢው ደመወዝ በወቅቱ ባለመከፈሉ ምክንያት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች በክትትሉ ወቅት ዝግ እንደነበሩ ኮሚሽኑ ተመልክቷል። በዚህም በሾኔ ከተማ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ለመማር ከተመዘገቡ ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፣ በምሥራቅ ባድዋቾ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለመማር ከተመዘገቡ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች፣ በምዕራብ ባድዋቾ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከተመዘገቡ ከ27 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንዲሁም በጎምቦራ ወረዳ ለመማር ከተመዘገቡ 28 ሺህ በላይ ተማሪዎች በክትትሉ ወቅት ከትምህርት ገበታ ውጪ ነበሩ፡፡

በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት ጋር በተያያዘ በምርመራው በተሸፈኑት የሾኔ ከተማ አስተዳደር፣ ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ፣ ምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ እና ጎምቦራ ወረዳ ውስጥ የሚሠሩ ከ 9ሺህ በላይ የመንግሥት ሠራተኞች ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተቆራረጠ ክፍያ እና ከነሐሴ ወር ጀምሮ ምርመራው እስከተከናወነበት ጊዜ ድረስ ደመወዝ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምክንያት ለከፋ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች መጋለጣቸውን መረዳት ተችሏል። ሠራተኞቹ ሌላ ገቢ እንደሌላቸውና ደመወዝ በመቋረጡ ምክንያት ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው የዕለት ጉርስ ለማግኘት እንደተቸገሩ፣ የቤት ኪራይ መክፈል እንዳልቻሉ፣ ከደመወዝ ጋር በተያያዘ በሚስተዋሉ ችግሮች ምክንያት ብድርም ማግኘት እንዳልቻሉ፣ በአካባቢው ያሉ የብድር እና ቁጠባ ተቋማት ለመንግሥት ሠራተኞች ብድር መስጠት እንዳቋረጡ እና ሕይወታቸውን ለማቆየት የቤት እቃ ከመሸጥ ጀምሮ በተለያዩ የጉልበት ሥራዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ለኢሰመኮ ገልጸዋል።

ምርመራው በተደረገባቸው የሃዲያ ዞን አከባቢዎች ከደመወዝ አለመከፈል ጋር ተያይዞ ቅሬታ እና ተቃውሞ ባሰሙ ሰዎች ላይ ማስፈራራት፣ ዛቻ፣ ድብደባ እና ለተለያዩ ጊዜያት እስራት ጭምር እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል።

ስለሆነም፣ ሁሉም የክልል መስተዳድሮች ተገቢ የማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ለሠራተኞች ደመወዝ ወቅቱን ጠብቆ መከፈሉን እና ሰብአዊ መብቶቹ መከበራቸውንና መጠበቃቸውን ሊያረጋግጡ ይገባል። ይህ ምርመራ ከተደረገበት ወቅት ጀምሮ በክልሎች ያለውን የደመወዝ ክፍያ ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ እርምጃዎች በመወሰድ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ሆኖም ለጉዳዩ የተሟላ ትኩረት በመስጠትና በተለይም በዚህ መግለጫ እንደተመለከተው ችግሩ በይበልጥ በታየባቸው የክልልና የዞን አስተዳደሮች ልዩ ትኩረት በማድረግ ዘላቂ መፍትሔ ማመቻቸት፣ አገልግሎት ያቋረጡ የጤና እና የትምህርት ተቋማትን ወደ ሥራ መመለሳቸውን ማረጋገጥ እና ለወደፊቱም ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት አስቀድሞ መከላከል ይገባል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ክፍያ መዘግየት እና ያለመከፈል ችግርን አስመልክቶ የተከናወነ የምክረ ሐሳቦች ትግበራ ክትትል ሪፖርት

Related posts

January 2, 2024April 10, 2024 Press Release
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፡- በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የተከሰተው ውጥረት እና ግጭት ከመባባሱ በፊት አስቸኳይ ምላሽ ይሻል
October 3, 2022October 5, 2022 Event Update
በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚሠሩ ሴት ሠራተኞች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እንዲሻሻል ባለግዴታዎች የበኩላቸውን ድርሻ የመወጣት ኃላፊነት አለባቸው
June 9, 2023August 28, 2023 Press Release
በግሉ የጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለሕብረተሰቡ በፋይናንስ ተደራሽ እንዲሆኑ የአሠራር፣ የፖሊሲ እና የሕግ ማሻሻያ ያስፈልጋል
August 8, 2024August 9, 2024 Event Update
በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ የሚገኘውን ትምህርት የማግኘት መብት በተመለከተ የተካሄደ የምክክር መድረክ

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.