እ.ኤ.አ. ከ2019 ጀምሮ በየዓመቱ ጥር 4 የሚታሰበውን የዓለም ብሬል ቀን በማስመልከት ብሬል ለዐይነ ስውራን እና ለከፊል ዐይነ ስውራን አስፈላጊ የመገናኛ ዘዴ በመሆኑ መንግሥታት ለብሬል ትምህርት እና ቁሳቁሶች መስፋፋት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥሩ የቀረበ ጥሪ
On World Braille Day, marked since 2019, a call for appropriate measures to create a conducive environment for expanding braille literacy
በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች የትምህርት እድል፣ የጤና እንክብካቤ፣ የሥራ ዕድል፣ ማኅበራዊ ጥበቃ አለማግኘትን እንዲሁም በማኅበረሰቡ ዘንድ ከተንሰራፋው የተዘባ አመለካከት በሚመነጩ እንቅፋቶች ምክንያት የሚደርስ መድልዎን ጨምሮ በርካታ ተግዳሮቶች ይገጥሟቸዋል
Persons with disabilities (PwDs) in Ethiopia, face numerous challenges including lack of access to education, health care, employment, social protection, and discrimination due to attitudinal barriers prevalent in the community
ዲስሌክሲያ ያለባቸው ሰዎች የመማር እና እኩል ዕድል የማግኘት መብቶች ያሏቸው ቢሆንም አብዛኛዎቹ ሰብአዊ መብቶቻቸውን ለመጠቀም ትልቅ እንቅፋት ይገጥማቸዋል
ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ ያለው አረጋውያን ፍላጎታቸውን እና ሁኔታቸውን ያገናዘበ የሕግ እና የፖሊሲ ማእቀፍ በመዘርጋት ሰብአዊ መብቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ እንዲጠቀሙ ማስቻል አስፈላጊ ነው
የምልክት ቋንቋን ይፋዊ የሥራ ቋንቋ ማድረግ መስማት የተሳናቸውን ሰዎች መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ፣ በማኅበረሰብ ውስጥ በሁሉም ዘርፍ የሚኖራቸውን የተሳትፎ መጠንና የአገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ ብሎም ሰብአዊ መብቶቻቸው ሙሉና ውጤታማ በሆነ ደረጃ እንዲረጋገጡ ለማስቻል አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው
በኢትዮጵያ ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ የማስፈጸሚያ ሕግ ሊወጣለት ይገባል
ከኢትዮጵያ የብሔር ብዝኃነት አንጻር ተጨማሪ ቋንቋዎችን በሥራ ቋንቋነት ለማካተት የሚያስችል የቋንቋ ፖሊሲ በቀረጻ ሂደት ላይ መሆኑ ቢታወቅም፤ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የግድ አስፈላጊ የሆነውን የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ለማድረግ በቂ ትኩረት አላገኘም
ይህን ውስን ሃብት ብሎም ዘርፉን የሚያስተዳድር የሕግና የፖሊሲ ማዕቀፍ ያስፈልጋል፡፡ ነፃነቱ የተጠበቀ ተቋም ማደራጀት፣ ግልጽና ገለልተኛ የፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሥርዓት መዘርጋት፣ ባለቤትነትንና ብዝኃነትን መወሰን፣ የይዘት ክትትል ሥርዓትን መደንገግ፣ የፕሮግራም ደረጃ ማስቀመጥ ያስፈልጋል