Skip to content
Facebook Twitter
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s and Children’s Rights
        • HR Monitoring & Investigation
        • Human Rights Education
        • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

የሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች አሠራር ሰብአዊ መብቶችን ሊያከብር ይገባል

November 11, 2022November 11, 2022 Press Release, Report

የተሟላ አዲስ የሕግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ወይም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ እንዲሻሻል ያስፈልጋል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Download Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ሠራተኞች ላይ የተሠሩ ጥናቶችን እና የቀረቡለትን በርካታ ቅሬታዎችን መሰረት በማድረግ ያከናወነውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ባለ 58 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል። በክትትል ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሠሩ በተለይም በሃዋሳ፣ ባሕር ዳር፣ አዲስ አበባ እና ጅማ ከተሞች፤ በአጠቃላይ 122 ሠራተኞች (83 ወንድ እና 39 ሴት)፣ 18 የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች፣ 25 ተጠቃሚ ድርጅቶች፣ 19 አግባብነት ያላቸው የመንግሥት ኃላፊዎች፣ 10 ሌሎች ባለድርሻ አካላት እና 6 የሠራተኞች ማኅበራት አመራሮችን በማሳተፍ መረጃዎች ተሰብስበዋል ። 

ክትትሉ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ስምምነት፣ በዓለም አቀፉ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት እና ሌሎች ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች፣ በዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ስምምነቶች እና የውሳኔ ሃሳቦች እና ሌሎች ተዛማጅ የሕግ ሰነዶችን ጨምሮ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ-መንግሥት እና በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ እውቅና የተሰጣቸው የሠራተኞች መብቶች ላይ መሰረት በማድረግ መከናወኑ በሪፖርቱ ተብራርቷል፡፡ 

ሪፖርቱ በግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች መብቶች አተገባበር ላይ ከፍተኛ ክፍተት መኖሩን ያመላክታል። በተለይም በእነዚህ ኤጀንሲዎች ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች ለሚሠሩት ሥራ በቂ ክፍያ የማያገኙ በመሆናቸው፤ በተለያዩ ሕጎች እውቅና ያገኘው በቂ ክፍያ የማግኘት መብታቸው እየተከበረላቸው እንዳልሆነ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ በአንዳንድ ተጠቃሚ ድርጅቶች በቀጥታ ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች እና በተመሳሳይ መደብና ቦታ በኤጀንሲዎች አማካኝነት ተቀጥረው በሚሠሩ ሠራተኞች መካከል ከፍተኛ የሆነ የክፍያ እና የጥቅማ ጥቅሞች ልዩነት መኖራቸውን ይህም አሠራር ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያ የማግኘት መርሕን እንደሚጻረር በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

ሠራተኞች በተገደበ የሥራ ሰዓት የመሥራት መብት ያላቸው ቢሆንም  የኤጀንሲ ሠራተኞች በተለይም ሴቶችን ጨምሮ የጥበቃ አገልግሎት በመስጠት ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች  በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጁ ከተደነገገው በቀን 8 ሰዓት እና በሳምንት 48 ሰዓት ያልበለጠ የመሥራት ግዴታ በላይ ያለትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዲሠሩ እንደሚገደዱ ሪፖርቱ አመላክቷል። 

ሠራተኞችን ከጉልበት ብዝበዛ ለመጠበቅ የሚያስችሉ ዕረፍት እና ፈቃድ የማግኘት መብት በሕግ የተረጋገጡ ቢሆንም በጥበቃ ሥራ የተሰማሩት ሠራተኞች የሳምንት የዕረፍት ቀን እንደሌላቸው እና ዕረፍቱን ሊተካ የሚችል የማካካሻ ክፍያ እንደማይከፈላቸው፣  ያለ በቂ ክፍያ  በሕዝብ በዓላት እንዲሠሩ እንደሚደረጉ፣  በአንዳንድ ኤጀንሲዎች  ሠራተኞቹ የዓመት እረፍት ፈቃዳቸውን ለመውሰድ  በቅድሚያ ተተኪ ሠራተኛ እንዲያመጡ እንደሚደርጉ፣ የሕመም ፈቃድ እና የልዩ ፈቃድ  እንደማይሰጥ እና የሚወስዱት ፈቃድ ከዓመት ፈቃዳቸው ላይ ተቀናሽ የሚደረግባቸው መሆኑ በሪፖርቱ ከተለዩ አሳሳቢ ጉዳዮች መካከል ናቸው። እንዲሁም በሃዋሳ ከተማ በተደረገው ክትትል ሠራተኞች የወሊድ ፈቃድን ከሙሉ ክፍያ ጋር እንደማያገኙ እና ከወሊድ  ሲመለሱም በፊት ይዘውት የነበረውን የሥራ መደብ እና ጥቅማ ጥቅም መልሰው ማግኘት እንደማይችሉ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ምንም እንኳን የኤጀንሲ ሠራተኞች እየተሰማሩባቸው ያሉ የሥራ ዓይነቶች በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 10(1) መሰረት እንደተወሰነ ጊዜ ወይም እንደተወሰነ ሥራ የማይቆጠሩ ቢሆንም፤ ሠራተኞቹ  የሚፈርሙት የሥራ ውል ግን የተወሰነ ጊዜ የሥራ ውል (የአንድ ወይም የሁለት ዓመት) በመሆኑ ሠራተኞቹን የሥራ ዋስትና እንዳይኖራቸው አድርጓል ። 

የመደራጀት መብት ሠራተኞች መብቶቻቸውን በኅብረት ለማስጠበቅ እና የተሻለ የሥራ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያስችል መብት ቢሆንም የኤጀንሲ ሠራተኞች ማኅበራት በተሟላ ሁኔታ አለመቋቋሙ እና  ሠራተኞቹ ትርጉም ያለው ቅሬታ የማሰሚያ እና ውጤታማ ፍትሕ የማግኛ ሥርዓት ተጠቃሚ አለመሆናቸው በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ከላይ ለተመለከቱት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የሠራተኞች ስለመብቶቻቸው እና መብቶቻቸውን ስለሚያስከብሩባቸው መንገዶች በቂ ግንዛቤ የሌላቸው መሆኑ፣ አብዛኞቹ የኤጀንሲ ሠራተኞች የሠራተኛ ማኅበር የሌላቸው መሆኑ፣ በማኅበር የተጠቃለሉ የኤጀንሲ ሠራተኞች ከግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር የኅብረት ስምምነት ያልተፈራረሙ መሆኑ፣ የአሠሪ እና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የሚመለከታቸው ጉዳዮች የወል የሥራ ክርክሮች ላይ ብቻ የተገደበ መሆኑ፣ አንዳንድ ኤጀንሲዎች የሠራተኞች ማኅበራት አመራሮች ላይ የሚያደርሱት ጫና መኖሩ፣ ለአሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርድ የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑ፣ ደካማ የቁጥጥር እና ክትትል ሥርዓት መኖር፣ የተለያዩ እና ያልተናበቡ ሕጎች መኖር፣ ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ አለመኖር እና ሕጋዊ ያልሆኑ ኤጀንሲዎች መስፋፋት፣ ተጠቃሚ ድርጅቶች ዋና ትኩረታቸው ዝቅተኛ ዋጋ የሚያቀርብ ኤጀንሲ ማግኘት ላይ መሆኑ እንዲሁም ኤጀንሲዎችም ዝቅተኛ ዋጋ የሚያቀርቡ መሆኑ እንደ አብይ ምክንያቶች ተጠቅሰዋል፡፡           

ኢሰመኮ በግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞችን መብቶች በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆኑ ለማስቻል በመብቶች አተገባባር ላይ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ለማስወግድ ያስችላሉ ያላቸውን ምክረ-ሃሳቦችን በሪፖርቱ አቅርቧል። በተለይም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጁ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የሚሸፍን እንጂ የሦስትዮሽ ግንኙነቶችን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ባለመሆኑ እና ይህም ለሠራተኞች ሰብአዊ መብቶች መጣስ አስተዋጽዖ እያበረከተ በመሆኑ በዚህ ዓይነት የሥራ ግንኙነት ውስጥ የሚሳተፉትን እያንዳንዱን አካላት ግዴታ እና የመንግሥትን ኃላፊነት በግልጽ የሚያስቀምጥ የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲን የሚመለከት ራሱን የቻለ ሕግ እንዲወጣ ወይም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ይህንን ባካተተ መልኩ እንዲሻሻል አሳስቧል።

የኢሰመኮ ማኅበራዊና ኢኮኖሚ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጅብሪል፣ በግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች መብቶችን አፈጻጸም በበላይነት የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግሥት ቢሆንም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተለይም የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች፣ ከግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ሠራተኞችን የሚያገኙ ተጠቃሚ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን እና ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ኢሰመኮ ያቀረባቸውን ምክረ-ሃሳቦችን በመተግበር ለሠራተኞቹ መብቶች መከበር የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሙሉ ሪፖርቱ እና አባሪዎች እዚህ ተያይዘዋል
Location Ethiopia

Related posts

June 5, 2022October 6, 2022 Explainer
በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ተፈጽሟል የሚባል ወንጀል እና ቅድመ ክስ እስር
March 24, 2022February 14, 2023 EHRC on the News
በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ግድያ ላይ የተጀመረው የእርቅ ሂደት “ተጠያቂነትን ሊያደናቅፍ” እንደማይገባ ኢሰመኮ አሳሰበ – Ethiopia Insider
September 9, 2022October 7, 2022 Human Rights Concept
The Human Rights of Workers
December 10, 2021December 10, 2021 EHRC Quote
Join us and Stand Up for Human Rights on Human Rights Day

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
EHRC
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org

© 2023 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Women’s & Children’s Rights
    • HR Monitoring & Investigation
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.