Situation of refugees, particularly in Gambella Region, dire and at serious risk of hunger and malnutrition
በማቆያ ማእከሉ እንዲገቡ ስለሚደረጉ ሰዎች አያያዝ እና ስለ ግዳጅ አሠራሩ ኢሰመኮ ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ክትትል እና ውትወታ በማድረግ የሰጣቸውን ምክረ ሐሳቦች በማስታወስ፣ ይህንን የግዳጅ አሠራር በአፋጣኝ ከማስቆም በተጨማሪ ለችግሩ ዘለቄታዊ እና ሁሉን አቀፍ የፖሊሲ ምላሽ ይሻል
የኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል መቀጠሉ አስፈላጊ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ለኮሚሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል
ከአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታው ጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት በተጨማሪ የፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ ወቅት ክትትል (Parliamentary Oversight) እና የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል የማድረግ ኃላፊነት ሊረጋገጥ ይገባል
በክልሉ የተሰማራውን ከፌዴራል እና ከክልሉ የጸጥታ አካላት የተውጣጣ ኃይል ማጠናከር እና አስፈላጊውን ድጋፍ ከመስጠት ተግባር ጎን ለጎን፣ ከነዋሪዎች፣ ከስደተኞች ተወካዮች፣ ከተቀባይ ማኀበረሰብ ተወካዮች፣ ከፌዴራል እና ጋምቤላ ክልል ጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም በስደተኞች አያያዝ ላይ በሚሠሩ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች የተውጣጣ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኃይል ማዋቀር አስፈላጊ ነው