ስብሰባው የሚካሄድበት ቀን ከእ.ኤ.አ. 2010 ጀምሮ መጋቢት 15 ቀን የሚታሰበው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ እውነቱን የማወቅ መብት እና የተጎጂዎች ሰብአዊ ክብር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታሰብበት ዕለት ነው
ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን በምናስብበበት በዚህ ወር ውስጥ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ማሻገር በሴቶችና ሕፃናት ላይ ሰብአዊ መብቶች ጥሰት እያደረሰ በመሆኑ ምላሽ ለመስጠት የሚደረጉ ጥረቶችን ውጤታማ ለማድረግ በጋራ መስራት አስፈላጊነትን ማስታወስ ተገቢ ነው
ትኩረት በሚሹ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል
ከየካቲት 17 እስክ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አባባ በተካሄደው ስብሰባ ከተሳተፉ መንግስታዊ ባለድርሻ አካላት ጋር የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን መብቶች ለማስጠበቅ እና ለማስከበር የሚረዳ ተቋማዊ መዋቅሮች እና ቅንጅታዊ አሰራሮች ሊዘረጉ የሚቻልባቸው ምቹ ሁኔታዎችን ስለመፍጠር ውይይት ተደርጓል።
ኮሚሽኑ ዓላማውን ለማስፈጸም ከሚሰራቸው ሰብአዊ መብቶችን የማስተማር እና የማስፋፋት ስራ ውጤታማ እንዲሆን ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በአጋርነት የሚሰራ ሲሆን፣ ከሀገራዊ የኪነጥበብና የሥነ ጥበብ ባለሞያዎችና ማኅበራት ጋር የሚያደርገውን ትብብር በተመሳሳይ መልኩ እኩል ክብደት የሚሰጠው ነው
ለሁለት ቀናት የሚካሄደው የውይይት መድረክ ሲገባደድ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሚናና የስራ ኃላፊነት ተሻሽሎ በወጣው መመሪያ መሰረት በመለየት ሁለተኛውን ውድድር ለማከናውን የወጣውን መርኃ ግብር ለመተግበር የጋራ መግባባት ላይ የሚደርሱበት እንደሚሆን ይጠበቃል
አበረታች ለውጦች ያሉ ቢሆንም፣ ክፍተቶችን ለማሻሻል የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል
የምክክር መድረኩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን መብቶች ለማስጠበቅና መብቶቻቸው መከበራቸውን ለማረጋገጥ የሚረዱ የሕግ ማዕቀፎች እንዲጸድቁ፣ እንዲተገበሩና ተመጣጣኝ ተቋማዊ መዋቅሮች እና አሰራሮች እንዲዘረጉ፣ እንዲሁም ክፍተቶች እንዲቀረፉ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው
ኢሰመኮ ባለፉት አራት ሳምንታት ስላካሄዳቸው ዋና ዋና ዝግጅቶች የበለጠ መረጃ እዚህ ያግኙ
“ውይይቱ በተለይም ከባለድርሻ አካላቶች ጋር በክትትሉ የተለዩ ክፍተቶችን ለማረም መግባባት ላይ ለመድረስ ያስቻለ ነው”