የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ያሉባቸውን ችግሮች በመስማትና በመሰነድ የሚመለከታቸውም ተቋማት መላ እንዲያፈላልጉላቸው ያለመ ውይይት ተካሂዷል
በአማራ ክልል እየተባባሰ የመጣው የትጥቅ ግጭት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከትል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እየተባባሰ የመጣውን የትጥቅ ግጭት እና የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም አማራጭ ቅድሚያ እንዲሰጠው ጠይቋል
በአማራ ክልል በመከላከያና በታጣቂ ሚሊሻዎች፣ ፋኖ የተነሳው ግጭት መባባሱን ተከትሎ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
ሁሉም ወገኖች ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ለሰላም አማራጮች ቅድሚያ እንዲሰጡ፣ ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ፣ የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎች በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ነዋሪዎችን ለበለጠ ጉዳት እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይዳርጉ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ ያሳስባል
በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የሰላም መደፍረስ፤ ካለኝ የተመጠነ በጀት እና የሰው ሀይል በላይ በስራ እንድወጠር አድርጎኛል ሲል ኢሰመኮ ተናገረ
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተቀበሩና የወዳደቁ ፈንጂዎች በአፋር ክልል 27 ሰዎችን፣ በአማራ ክልል ቁጥራቸው ያልተገለፀ ሰዎችን ለሞት እንዲሁም ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
በሰው የመነገድ ወንጀል ማለት ግለሰቦችን ለብዝበዛ በማስገደድ፣ በመጥለፍ፣ በማታለል ወይም በኃይል በመመልመል፣ በማጓጓዝ፣ በማሸጋገር፣ በመቀበል፣ ወይም በማስጠለል የሚፈጸም ድርጊት ነው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተቀበሩ ፈንጂዎችን የማጽዳቱ ሥራ በአስቸኳይ መጠናቀቅ እንደሚኖርበት አሳስቧል
በሰው የመነገድ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ሰዎች ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ የተሟላ ድጋፍ እና ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ