አጠቃላይ መርሖች እነዚህ የመመሪያ መርሖች፡- (ሀ) ሰብአዊ መብቶችን እና መሠረታዊ ነጻነቶችን የማክበር፣ የመጠበቅና የማሟላት ነባር የመንግሥት ግዴታዎችን፤ (ለ) የንግድ ድርጅቶች እንደ ልዩ የኅብረተሰብ አካል ልዩ ተግባራትን የማከናወን ሚና ሲወጡ ሁሉንም የሚመለከታቸው ሕጎችን እና ሰብአዊ መብቶችን በማክበር እንዲሆን ተጠባቂነትን፤ (ሐ) መብቶች እና ግዴታዎች በሚጣሱበት ጊዜ ተገቢና ውጤታማ ከሆኑ መፍትሔዎች ጋር እንዲጣጣሙ የማድረግ አስፈላጊነትን ዕውቅና በመስጠት የተመሠረቱ...