በማንኛውም ምክንያት ቢሆን የሚታወጅ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ለሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው። ኢሰመኮ በተለያዩ ወቅቶች በሀገሪቱ በከፊልም ሆነ በሀገር አቀፍ የተጣሉ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች በመቋቋሚያ አዋጁ በተጣለበት ኃላፊነት መሠረት ክትትል እና ምርመራ አድርጎ፣ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። በእነዚህ የክትትል እና የምርመራ ግኝቶቹም መሠረት ከዚህ ቀደም...