የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኅዳር ወር 2015 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች አተገባበር የክትትል ሪፖርት ላይ ያቀረባቸውን ምክረ ሐሳቦች ተፈጻሚነት አስመልክቶ ከመስከረም 6 እስከ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. የትግበራ ክትትል በማከናወን ያዘጋጀውን ባለ 12 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ኢሰመኮ በዚህ የትግበራ ክትትል በዋናው የክትትል ሪፖርት የተጠቆሙ ምክረ ሐሳቦች...