ይህ ቻርተር ከአሕጉራችን የሰብአዊ መብት ሰነዶች ቀዳሚው ነው፡፡ ይህን ቻርተር ፈርመው የተቀበሉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል ሀገራት በዚህ ቻርተር የተደነገጉትን መብቶች፣ ግዴታዎችና ነጻነቶች አውቀው በመቀበል ለተግባራዊነታቸው ሕግ ለማውጣትና ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ ግዴታ ገብተዋል፡፡
የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደኅንነት ቻርተር፡፡ የቻርተሩ ተዋዋይ ሀገራት የሆኑ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል ሀገራት በቻርተሩ ለተደነገጉ መብቶች፣ ነጻነቶችና ግዴታዎች ዕውቅና የመስጠት የቻርተሩ ድንጋጌዎችን ተፈጻሚ ለማድረግ በቻርተሩና በየሕገ-መንግሥቶቻቸው በተመለከቱ ድንጋጌዎች መሰረት እንደ አስፈላጊነቱ የሕግ ማውጣትን እና ሌሎች እርምጃዎች የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፡፡


በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዐይነ ሥውራን፣ የንባብ የዕይታ ችግር ላለባቸው እና በመደበኛ የንባብ ስልት ለማንበብ አካላዊ ችግር ላለባቸው ሰዎች የቀለም ጽሑፍ ህትመት ሥራዎች ተደራሽነትን ለማመቻቸት የወጣውን የማራካሽ ስምምነት በአዋጅ ቁጥር 1181/2012 በማጽደቁ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነዶችን በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ለመተርጎም እና ለማሰራጨት በአዋጅ ቁጥር...