- Version
- Download 39
- File Size 348.57 KB
- File Count 1
- Create Date October 17, 2022
- Last Updated October 17, 2022
ሁሉም ዓይነት የዘር ልዩነቶች ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር በተፈጥሯዊ የሰው ልጅ ክብርና እኩልነት መርሆዎች መመስረቱን፤ እንዲሁም ሁሉም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገራት ድርጅቱ የተመሰረተበት ዓላማ፤ ማለትም ምንም ዓይነት የዘር፣ የቀለም፣ የጾታ፣ የቋንቋ ወይም የሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግ የማንኛውም ሰው ሰብአዊ መብቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስከበርና ለማጋገጥ ከድርጅቱ ጋር በመተባበር በግልና በጋራ እርምጃ ለመውሰድ የገቡትን ቃል ኪዳን ግምት ውስጥ በማስገባት።