የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በበዓሉ ላይ የተከሰቱትን ክስተቶች አስመልክተው በሰጡት ሀሳብ፣ የጸጥታ ኃይሎች በዓሉን ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ከልክ ያለፈ አላስፈላጊ ድብደባ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ ጥይትና ሌሎች ከመጠን ያለፉ እምጃዎችን መውሰዳቸውን ጠቁመዋል
Implicated law enforcement officials must be subject to accountability and law enforcement officers should be adequately trained to avoid similar incidents
ከሰብአዊ መብቶች አኳያ ሊቀጥሉ እና ሊበረታቱ የሚገባቸው መልካም አሠራሮች ቢኖሩም የአረጋውያን መንከባከቢያ ማእከላቱ በአብዛኛው ቋሚ የገቢ ምንጭ የሌላቸው እና በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎም ውስን መሆኑ አገልግሎታቸውን ለማስቀጠልና ዘላቂነቱን (sustainability) ለማረጋገጥ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል
የመንግሥት የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር አካላት በሙሉ በበቂ ምክንያት በወንጀል የተጠረጠረን ሰው በተለይም በቅድመ ምርመራ ወቅት የዋስትና መብት አጠባበቅ ሥርዓትን ባከበረ መንገድ ምርመራ ከማድረግ ውጪ ተገቢ ያልሆነ እስርን ማስወገድ አለባቸው
ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ዋና ኮሚሽነር ዳኤንል በቀለ (ዶ/ር) ፈርመዋል
ስምምነቱ የሰብአዊ መብቶች እሴቶችን ወደ ማኅበረሰቡ ከማስረጽ አኳያ ተደራሽነትን በመጨመር በኢትዮጵያ ዘላቂና ውጤታማ በሆነ መንገድ የሰብአዊ መብቶች ባህልን ለማስፈን ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት የሚያጋጥማቸውን የከባቢያዊ፣ የአመለካከት፣ የተግባቦት እና ተያያዥ ተቋማዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል