በነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም. በቆላ ሻራ ቀበሌ ለደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነት ማረጋገጥ እና ከኃይል እርምጃዎች መቆጠብን ጨምሮ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በአፋጣኝ ማስጀመር እና በሀገራዊ እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብት ሊረጋገጥ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው ሪፖርት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙርያ ወረዳ በሻራ ቀበሌ ባለፈው ነሐሴ ያልታጠቁ ሦስት ሰላማዊ ሰዎች ከሕግ አግባብ ውጪ መገደላቸውን አስታወቀ
የጤና መብት እና በግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት በተሻለ ሁኔታ እንዲተገበሩ ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሠሩና የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል
በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሥር የሚገኙ ኤልጎ፣ ወዘቃ፣ ደምብሌ እና ጫሞ 01 የተባሉ አራት ቀበሌዎች ከጋሞ ዞን በመውጣት ልዩ ወረዳ ሆነው ለመደራጀት በተለያየ ጊዜ ጥያቄ ሲያነሱ የቆዩ ሲሆን፤ በተለይ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ውዝግቡ እየተባባሰ እንደመጣ ተገልጿል
ከጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች እና በጋሞ ዞን አስተዳደር መካከል ያለው አለመግባባት ውጥረት እየጨመረ መምጣቱን አመላክቷል
ከግጭቶቹ ጋር በተያያዘ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች በቂ የሆነ አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ በአፋጣኝ ማቅረብን ጨምሮ፣ ተፈናቃዮች እና ነዋሪዎች ወደ ዘላቂ ሰላም የሚመለሱበት ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል
በአዲስ መልኩ በሚዋቀሩ አካባቢዎች የሚነሱ የደመወዝ እና ተያያዥ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት በጤና እና በትምህርት መብት እንዲሁም በአካባቢዎቹ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሉ ሥጋቶችን ይቀርፋል