EHRC has engaged key stakeholders to resolve the issue through dialogue and prioritizing human rights
ኢሰመኮ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና ከታገዱት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግ ለጉዳዩ መፍትሔ ለማስገኘት ሢሠራ ቆይቷል
ኢሰመኮ ባደረገው ጥረትም በአራቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ከዛሬ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ መነሳቱን አስታውቋል
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እግድ ጥሎባቸው የነበሩ አራት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የተጣለባቸው እገዳ መነሳቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል
ኢሰመኮ በሰብአዊ መብቶች ላይ ከሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በትብብርና በቅንጅት መሥራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚተላለፉ እገዳዎች የሲቪክ ምህዳሩን በማጥበብ በማህበር የመደራጀት መብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳይፈጥሩ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡ ኢሰመኮ፤ ተቋሟቱ የፈጸሟቸውን ከባድ የሕግ ጥሰቶች በዝርዝር ባላስቀመጠ ደብዳቤ መታገዳቸው አሳሳቢ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ነው ያለው
የሲቪል ማኅበራት ከኢሰመኮ ጋር የሚያደርጉት ትብብርና ቅንጅት ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ መሻሻልና መስፋፋት ሥራ ውጤታማነት ጉልህ አስተዋጽዖ አለው