የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እየተባባሰ የመጣውን የትጥቅ ግጭት እና የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም አማራጭ ቅድሚያ እንዲሰጠው ጠይቋል
በአማራ ክልል በመከላከያና በታጣቂ ሚሊሻዎች፣ ፋኖ የተነሳው ግጭት መባባሱን ተከትሎ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
ሁሉም ወገኖች ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ለሰላም አማራጮች ቅድሚያ እንዲሰጡ፣ ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ፣ የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎች በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ነዋሪዎችን ለበለጠ ጉዳት እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይዳርጉ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ ያሳስባል