በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሥር የሚገኙ ኤልጎ፣ ወዘቃ፣ ደምብሌ እና ጫሞ 01 የተባሉ አራት ቀበሌዎች ከጋሞ ዞን በመውጣት ልዩ ወረዳ ሆነው ለመደራጀት በተለያየ ጊዜ ጥያቄ ሲያነሱ የቆዩ ሲሆን፤ በተለይ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ውዝግቡ እየተባባሰ እንደመጣ ተገልጿል
ከግጭቶቹ ጋር በተያያዘ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች በቂ የሆነ አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ በአፋጣኝ ማቅረብን ጨምሮ፣ ተፈናቃዮች እና ነዋሪዎች ወደ ዘላቂ ሰላም የሚመለሱበት ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል