የመሬት መብት ከምግብ፣ ከጤና፣ ከመጠለያ፣ ከውሃ፣ ከባህላዊ መብቶች ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው በመሆኑ መሬት ነክ ድንጋጌዎችና ፖሊሲዎች ሰብአዊ መብቶች መር ሊሆኑ ይገባል
ቅድመ ማስለቀቅ፣ በማስለቀቅ ወቅት እንዲሁም ድኅረ ማስለቀቅ ጊዜ መንግሥት ሊያሟላ የሚገባቸው የሰብአዊ መብቶች መርሆችን ያልተከተለ ሲሆን በኃይል ማፈናቀል እንደተፈጸመ ይቆጠራል፡፡ ይዞታ የማስለቀቅ ተግባር በአጠቃላይ ሰዎችን ቤት አልባ እንዲሆኑ እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጋላጭ ማድረግ የለበትም