ሲቪሎችን ለሞትና ለአካል ጉዳት ከሚያጋልጡ ዕርምጃዎች በተጨማሪ፣ የዘፈቀደ ጅምላና የተራዘመ እስራት፣ የተፋጠነ የፍትሕ ዕጦት በኢትዮጵያ መበራከታቸውን ሪፖርቱ ይገልጻል
ግድያዎቹ የተፈጸሙት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም በክልሎቹ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች እንደሆነ ኢሰመኮ ዓርብ፣ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል
Commission calls for immediate release of detainees held incommunicado
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በግጭት ዐውድ ውስጥ ያሉ አካባቢዎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በአሳሳቢ ሁኔታ መቀጠላቸው በሪፖርቱ ገልጿል
ኮሚሽኑ እንደለጸው ሪፖርቱ ከመስከረም ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም. እስከ ታኅሣሥ 2017 ዓ.ም. አጋማሽ ባለው ጊዜ ውስጥ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ነው ብሏል፡፡ ሪፖርቱ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በሙሉ የሚሸፍን አይደለም ያለው ኮሚሽኑ በእነዚህ አካባቢዎች በነጻነት ተንቀሳቅሶ የተሟላ ክትትልና ምርመራ ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ፣ ውጤታማ ክትትልና ምርመራ የተከናወነባቸውን ጉዳዮች ብቻ በማሳያነት እንዳቀረበም ገልጿል
የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ፣ በመዘዋወር መብትና በመጓጓዣ መንገዶች ላይ የሚፈጸም ሕገ-ወጥ ገደብ፣ የሀገር ውስጥ መፈናቀል እና የዳኝነት ነጻነት መሸርሸሮች እንዳሉም ኢሰመኮ በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል
በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ “ቃሊቲ አካባቢ” ተብሎ በሚጠራው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ባለ 'ሰፊ መጋዘን' ውስጥ፤ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ሰዎችን የመያዝና ወደ ማቆያ ማዕከል የማስገባት ድርጊት አሁንም መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል
ምክረ ሐሳቦች እንዲፈጸሙ ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሠሩ፤ በክልሉ መንግሥት እየተወሰዱ ያሉ አበረታች እርምጃዎችም ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ከዚህ ቀደም ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ “የመንግሥት ጫና የለብንም። ከመጣም አንቀበልም” ሲሉ መልሰው ነበር