የተሻለ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እና በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅባቸዋል
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ም/ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት አባል ዶ/ር ካሣ ተሻገርን ጨምሮ 53 ሰዎች አዋሽ አርባ ውስጥ ባለ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ መታሰራቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አረጋገጠ
ኮሚሽኑ ይህን ያለው ዋና ኮሚሽነሩ ዳንዔል በቀለን ጨምሮ አምስት የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የሚገኙበት ቡድን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በቁጥጥር ሥር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. መጎብኘቱን አስመልክቶ ዛሬ ነሐሴ 27 ባወጣውና ለአሻም በላከላት መግለጫ ላይ ነው
በማረሚያ ቤቶች እና በፖሊስ ጣቢያዎች የታራሚዎችን እና የተጠርጣሪዎችን አያያዝ ለማሻሻል በኮሚሽኑ የሚሰጡ ምክረ ሐሳቦችን በቁርጠኝነት መፈጸም ያስፈልጋል
በፖሊስ ጣቢያዎች ያለውን የተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ለማሻሻል የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ትኩረት እና አፋጣኝ ምላሽ ይፈልጋል
በኦሮምያ ማረሚያ ቤቶች አሁንም ታራሚዎች ከፍተኛ የሆነ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ችግሮች እንዳሉባቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለፀ
በአማራ ክልል የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አካላት መሻሻሎችን አጠናክረው መቀጠልና የሚታዩ የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ጉድለቶችን ለማረም ትኩረት ሰጥተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል