በሰው የመነገድ ወንጀል ማለት ግለሰቦችን ለብዝበዛ በማስገደድ፣ በመጥለፍ፣ በማታለል ወይም በኃይል በመመልመል፣ በማጓጓዝ፣ በማሸጋገር፣ በመቀበል፣ ወይም በማስጠለል የሚፈጸም ድርጊት ነው
በሰው የመነገድ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ሰዎች ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ የተሟላ ድጋፍ እና ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ
ወንጀሉን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ረቂቅ የስትራቴጂ ዕቅድ ጸድቆ ወደ ሥራ ሲገባ የጥበቃና ድጋፍ ሥርዓት እንደሚዘረጋ ይጠበቃል