በኢትዮጵያም አረጋውያን ለመሰል የመብት ጥሰት ይጋለጣሉ የተባለ ሲሆን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተቋማት በአረጋውያን ዙሪያ እንዴት እየሰሩ እንደሆነ ምልከታ አደርጋለሁ ብሏል
አረጋውያን እነማን ናቸው? በአረጋውያን ላይ የሚደርስ ጥቃት ምን ማለት ነው? አረጋውያን ላይ የሚደርሱ የጥቃት አይነቶች ምን ምን ናቸው?
Older persons have the right to be protected from abuse and harmful traditional practice
አረጋውያን ከጥቃት እና ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የመጠበቅ መብት አላቸው
ውጤታማ እና ትርጉም ያለው የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎን ለማረጋገጥ የግምገማና የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት ቁልፍ ተግባራት ናቸው
ተማሪዎቹ አገልግሎት በሚያገኙባቸው ቢሮዎች ፣ በትምህርት እና መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች እና በሌሎች የመብት ጥሰት ይደርስባቸዋል ተብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በአምስቱ ላይ ባደረገው ክትትል፣ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ እንደሌላቸው ማረጋገጡን አስታወቀ
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣የመረጃና ተግባቦት እንዲሁም ከአመለካከት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ነጻ መሆን አለባቸው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ፤ በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ የአካል ጉዳተኞች የከፍተኛ ትምህርት ተካታችነትን ሁኔታ ለመፈተሽ ያስችለው ዘንድ የኢትዮጵያ የሕግ እና የፖሊሲ ማዕቀፎች እንዲሁም አጠቃላይ ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣ የመረጃ እና የአመለካከት ተደራሽነትን...
በባሕርይ እና በማኅበራዊ ለውጥ ዙሪያ የሚሠሩ አካላት ብዝኃነትን ማዕከል በማድረግ የአረጋውያንን እና የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ መብቶች በማስፋፋት ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው