ኢሰመኮ ባሕር ዳር እና ሃዋሳ ጽሕፈት ቤቶች: 

በግንቦት እና ሰኔ ወራት 2014 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕ እና የዴሞክራሲ ተቋማት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የኢሰመኮን ባሕር ዳር እና ሃዋሳ ጽሕፈት ቤቶች በመጎብኘት ከጽሕፈት ቤቶቹ ኃላፊዎች እና ባልደረቦች ጋር ውይይት አድርገዋል። የተከበሩት የምክር ቤቱ አባላት ኮሚሽኑ በተለያዩ ጽሕፈት ቤቶቹ አማካኝነት ያለውን ተደራሽነት ለማስፋት እና የተቋሙን የሰው ኃይል መዋቅርና ሌሎች ለውጦች የማስፈጸሙ ሂደት እስከ ጽሕፈት ቤቶች ድረስ ማከናወን መቻሉን አመስግነዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕ እና የዴሞክራሲ ተቋማት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የኢሰመኮን ሃዋሳ ጽሕፈት ቤቶ በመጎብኘት ላይ

በተጨማሪም ኮሚሽኑ በ2014 ዓ.ም. በጀት ዓመት ባስመዘገባቸው ውጤቶች ላይ ተመርኩዞ በሚቀጥለው በጀት ዓመት ተደራሽነቱን የበለጠ በማስፋት እና የሰው ኃይሉን በማጠናከር የበለጠ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ያላቸውን እምነት ገልጸው፣ ለዚህም ኮሚሽኑ የምክር ቤቱ ሙሉ ድጋፍ እንደሚኖረው አስረድተዋል።  

EHRC Jigjiga Office: 

Launch of Durable Solutions Strategy 2022-25 – For Internally Displaced Persons (IDPs) 

EHRC Jigjiga took part in the launch of the steering committee of the Durable Solutions Strategy 2022 – 2025 for IDPs held in the Somali Regional State in May 24, 2022.

According to IOM’s recent data, there are 4,509,081 IDPs in Ethiopia and the Somali Regional State hosts 932,568 IDPs. The Strategy developed by the regional government, United Nations International Organization for Migration (UNIOM) and various donors aims to support internally displaced communities in the process voluntarily, in safety and with dignity return of IDPs to their habitual residence, integration with the host community or relocation to other parts of the country. The strategy will be implemented with a focus on emergency humanitarian aid, climate change, peacebuilding, rehabilitation and social affairs, community service, agriculture and rural development.

The high-level event gathered ambassadors of Switzerland, Germany, Japan, Sweden, Finland, and Check Republic residing in Ethiopia. In addition, UN Resident and Humanitarian Coordinator, Country Directors of IOM, UNHCR and UNICEF and the president of Somali Regional State took part in the lunching event. The international partners expressed their commitment to support the efforts of stakeholders engaged in finding durable solutions in matters related to IDPs. 

EHRC was involved from the inception of the strategy to its formulation and will continue to do so. 

EHRC Jigjiga Office: 

EHRC Jigjiga Office marked World Refugee Day at the Shader Refugee Camp

On June 20, 2022 the Ethiopian Human Rights Commission Jigjiga Office in collaboration with United Nations High Commissioner for Refugees (UNHCR), Refugees and Returnees Services (RRS), RCC, CBO, and Shader community marked World Refugee Day at the Shader Refugee Camp, in the Somali Regional State. 

During the observance, EHRC together with IMC and UNHCR organized an interactive question and answer session for women program in IMC Wellness Center at Shader refugee camp. The session aimed at creating awareness about the plight of refugees and shedding light on the challenges they face on a daily basis. It also introduced EHRC’s key strategic intervention areas which include research and advocacy; empowerment of vulnerable communities to claim their rights; monitoring compliance with national and international standards as well as partnership with stakeholders to advance the rights agenda as well as protection needs of these segments of society.

Shader Refugee Camp

As Ethiopia is one of the largest refugee hosting countries in the world, has a significant population of internally displaced persons (IDPs) and is a source, transit and destination for many migrants, ensuring the promotion, respect and protection of the rights of refugees, IDPs and migrants is one of the critical priorities. On the occasion, EHRC conveyed this message and assured its commitment to promote and protect the rights of Refugees to the residents of three camps in Fafan Zone of the Somali Regional State.

In addition, other similar events related to World Refugee Day have taken place in Qabribayah and Aw bare Refugee Camps of the Somali Regional State.   

World Refugee Day is designed to celebrate and honour refugees from around the world. This year, the focus of World Refugee Day is the ‘Right to Seek Safety’. It is a reminder that everyone, despite where they are from, who they are and whenever they are forced to flee, has the right to seek safety.

ኢሰመኮ ባሕር ዳር 

በአማራ ክልል በሚገኙ በተመረጡ 10 ማረሚያ ቤቶች እና 25 በፖሊስ ጣቢዎች የሚገኙ የተጠርጣሪ ሰዎች እና የታራሚዎች አያያዝና ሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ሁኔታ ላይ በተደረገ ክትትል ግኝቶች እና ምክረ-ሃሳቦች ዙሪያ ከፖሊስ፣ ከማረሚያ ቤቶች እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገ ውይይት

የኢሰመኮ የባሕርዳር ጽሕፈት ቤት በክልሉ በሚገኙ 10 ማረሚያ ቤቶች እና 25 ፖሊስ ጣቢያዎች የታራሚዎችን እና የተጠርጣሪዎችን አያያዝና ሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ በሚመለከት ከመጋቢት 2 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ የክትትል ሥራ አከናውኗል፡፡ በዚሁ መሰረት በክትትል ሪፖረት በተለዩ ግኝቶች እና በተሰጡ ምክረ ሃሳቦች ላይ ክትትል ከተደረገባቸው ማረሚያ ቤት ኃላፊዎች፣ ክትትል ከተደረገባቸው ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች፣ በክልሉ ከሚገኙ ማረሚያ ቤት ኃላፊዎች፣ ከሁሉም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች፣ በክልል ደረጃ ከሚገኙ የሚመለከታቸው የፖሊስ እና ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር በደብረ ታቦር ከተማ የውይይት መድረክ በማዘጋጀት የክልሉ ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በተገኙበት ሰኔ 24 እና 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ውይይት ተደርጓል።  

የሁለት ቀናት የውይይት መድረኮች የማረሚያ ቤቶች ውይይት በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ እና በኢሰመኮ ባሕር ዳር ጽ/ቤት ኃላፊ የተመሩ ሲሆን፣ የፖሊስ ጣቢያዎች ውይይት ደግሞ በጽ/ቤቱ ኃላፊ እና በሰብአዊ መብቶች ምርመራና ክትትል አስተባባሪ ተመርተዋል። በውይይት መድረኩ ላይ በክትትሉ የታዩ ጠንካራ ጎኖች፣ ደካማ ጎኖች፣ የታዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እና ምክረ-ሀሳቦችን ያካተቱ ሁለት የክትትል ሪፖርቶች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርገውባቸዋል። በአብዛኛው በግኝቶች እና በምክረ-ሀሳቦች ላይ መግባባት ላይ ተደርሶ በውይይቶች መጨረሻ ተሳታፊ የነበሩ የፖሊስ እና የማረሚያ ቤት ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ምክረ-ሃሳቦችን እንዴት እና መቼ መፈጸም እንዳለባቸው እቅድ በማዘጋጀት ውይይቶች ተጠናቀዋል፡፡ 

በፖሊስ ጣቢያዎች የተጠርጣሪዎች አያያዝና የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ረገድ የተወሰኑ መሻሻሎች መኖር እንደተጠበቀ ሆኖ በክትትሉ ሰፊ ችግሮች ተለይተዋል፡፡ በፖሊስ ጣቢያዎች ክትትል ወቅት የተለዩ ችግሮች በብዛት በህገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን ማሰር (ያለ ፍ/ቤት ትእዛዝ መያዝ፣ ምስክር የሆኑ ሰዎችን ማሰር፣ አቤቱታ የሚያቀርቡ ሰዎችን ማሰር፣ በፍትሐ ብሄር ጉዳይ ማሰር፣ በ48 ሰዓት ፍ/ቤት ሳያቀርቡ ማቆየትና ማሰር)፣ በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች ተጠርጣሪዎችን በእግር ብረት አስሮ ማስቀመጥ፣ በፖሊስ ጣቢያ ተጠርጣሪዎችን አስሮ ማቆየት፣ በተለያየ ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች ፈጣን ፍትህ አለማግኝት፣ በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች ተጠርጣሪዎች እንዲያምኑ ድብደባ መፈጸም እና በመያዝ ሂደት የፖሊስ አባላት ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል በመጠቀም በድብደባ ጉዳት ማድረስ ይጠቀሳሉ። እንደዚሁም በፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ ተጠርጣሪዎች ከቤተሰባቸው ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት ነጻነታቸውን የጠበቀ አለመሆን፣ የክልሉ መንግስት ከሁለት ዓመት በፊት በፖሊስ ጣቢያዎች ምግብ እንዲቀርብ ለአንድ ተጠርጣሪ ብር 36 የወሰነ ቢሆንም እስካሁን አንድም ፖሊስ ጣቢያ ለተጠርጣሪዎች ምግብ ባለማቅርቡ የሚራቡ ተጠረጣሪዎች መኖራቸው፣ በቂ የውሀ እና የጤና አገልግሎት አለመኖር፣ በፖሊስ ጣቢያዎች አልጋና ፍራሽ አለመኖር፣ ክፍሎች የተጨናነቁና ንጹሕ አለመሆን፣ የመጸዳጃ ቤቶች ጽዳት መጓደል እና ልዩ ትኩረት ለሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚደረግ ድጋፍ አለመኖሩ የሚጠቀሱ ችግሮች ናቸው፡፡

ሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. የፖሊስ ጣቢያዎች የክትትል ሪፖርት ላይ የተደረገ ውይይት

በተጨማሪ በየደረጃው ያለ የአስተዳደር አካል ለፖሊስ ጣቢያዎች በቂ ትኩረት አለመስጠት፤ በቂ በጀት፣ የሰው ኃይልና ቁሳቁስ አለመሟላት፤ የአስተዳደር አካላት ጣልቃ ገብነት እና የመብት ጥሰት በሚፈጽሙ የፖሊስ አባላት ላይ የሚወሰደው ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ አነስተኛ መሆን በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የተጠርጣሪዎች አያያዝ አለመሻሻል አስተዋጻዖ እንዳለው በውይይቱ ተነስቷል፡፡

በውይይቱ በማረሚያ ቤቶች በኩል በታራሚዎች አያያዝ እና ሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ መሻሻሎች እየታዩ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚታዩ የመብት ጥሰቶች እና የአያያዝ ጉድለቶች አንዲስተካከሉ ከመግባባት ተደርሷል። ከተነሱት ጉድለቶች መካከል ታራሚዎችን በካቴና አስሮ የሚያስቀምጡ ማረሚያ ቤቶች መኖራቸው፣ በአንዳንድ ታራሚዎች ላይ አካላዊ ድብደባ መፈጸሙ፣ በቀለም ትምህርት እና የሙያ ስልጠና የሴት ታራሚዎች ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑ፣ የይቅርታ አሰጣጥ መመሪያ ቢኖርም የአፈጻጸም ችግር መኖር፣ ታራሚዎችን በፈርጅ ለይቶ አለመያዝ፣ ወጣት ጥፋተኞችን ከአዋቂዎች ጋር ቀላቅሎ ማሰር፣ ከፍርድ በፊት የሚታሰሩ ሰዎች መበራከት በተለይም በጊዜ ቀጠሮ ታስረው ቀጠሮ ያለፈባቸው ሰዎች መኖር እና የምግብ አቅርቦት በቂ አለመሆን ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም አብዛኞቹ ማረሚያ ቤቶች ደረጃቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው የምኝታ ጥበትና የመኝታ አልጋና ፍራሽ አለመኖር፣ በቂ የሕክምና አገልግሎት አለመኖር፣ የታራሚዎች ዝውውር ፍላጎትን መሰረት ያደረገ አለመሆንና ከቤተሰቦቻቸው እርቆ በሚገኝ ማረሚያ ቤት ማሰር፣ ታራሚዎች በፍላጎታቸው ሲዛወሩ የአጃቢና የራሳቸው አበልና መጓጓዣ ወጪ በራሳቸው የሚሸፈን እንዲሆን የሚያደርግ አሰራር መኖር እና ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎችን ሰብአዊ መብቶች አስከብሮ ለመያዝና ለማረም በቂ በጀት፣ ቁሳቁስ እና የሰው ኃይል አለመኖር በጉድለት የሚጠቀሱ ግኝቶች መሆናቸው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ 

በአጠቃላይ በሁለቱም ተቋማት የተነሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና የአያያዝ ችግሮች በተሰጡት ምክረ-ሃሳቦች መሰረት መስተካከል የሚገባቸው መሆኑን እና አብዛኞቹ በፖሊስ አካላቱ መስተካከል የሚችሉ ሲሆኑ ሌሎችን የክልሉ የአስተዳደርን፣ የፍትሕና የፀጥታ ተቋማትን ድጋፍና ተሳትፎ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ለይቶ በማቅረብና በማረም ለመስራት በውይይት መድረኮች መግባባት ላይ ተድረሷል፡፡