Skip to content
Facebook Twitter YouTube Linkedin Flicker
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Human Rights Monitoring and Investigation
        • Women’s and Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚሠሩ ሴት ሠራተኞች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እንዲሻሻል ባለግዴታዎች የበኩላቸውን ድርሻ የመወጣት ኃላፊነት አለባቸው

October 3, 2022October 5, 2022 Event Update

ኢሰመኮ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሴት ሠራተኞች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ድኅረ ክትትል ግኝቶች ያቀረባቸው ምክረ ሃሳቦች ተፈጻሚነታቸው ሊረጋገጥ ይገባል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በመሥራት ላይ የሚገኙ ሴት ሠራተኞች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሳምንት በተደረገው ድኅረ ክትትል የተለዩ ግኝቶች ላይ መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ ከመንግሥት አስፈጻሚ አካላት፣ ከአዳማ ከተማ የፖሊስ አካላት፣ ከሚመለከታቸው ሲቪል ማኅበራት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ አስተዳደር ኃላፊዎች፣ የአሠሪዎችና የሠራተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽኖች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ውይይት አካሂዷል።

በድኅረ ክትትል ግኝቶች ላይ በተካሄደው ውይይት በክትትሉ የተለዩ ጠንካራና ትኩረት የሚሹ ክፍተቶች ለተሳታፊዎች ቀርበዋል፡፡ በጠንካራ ጎን ከተነሱት መካከል፣ ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና ተጠቃሚ መሆናቸው፣ የመደራጀት መብትን ለማስከበር በጎ ጅምሮች መኖራቸው፣ ከወሲባዊና ሥነ ተዋልዶ ጤና እንዲሁም የሕይወት ክህሎት ጋር የተያያዘ መረጃ የማግኘት መብትን ለማስጠበቅ መሠራቱ እና በፓርኩ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለሟሟላት በተለያዩ ተቋማት ቢሮዎች መመቻቸታቸው የሚጠቀሱ ናቸው። 

በሌላጎኑ በመንግሥት አካላት መደረግ ያለበት ቁጥጥር አነስተኛ መሆኑ፣ በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪ ዘርፉ የጤና ጉዳት የሚያስከትሉ ሥራዎችን ለመለየት የሚያስችሉ አሠራሮች አለመዘርጋት፣ ሕግን ያልተከተለ የሴት ሠራተኞች ቅነሳ መደረጉ እና ለትርፍ ሰዓት ሥራ የሚከፈለዉ ክፍያ አነስተኛና አስገዳጅ መሆኑ ውይይት ከተደረግባቸው ክፍተቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። በተጨማሪም ለነፍሰ ጡርና ለወለዱ ሴት ሠራተኞች የሚደረገው ድጋፍ በቂ አለመሆኑ፣ ከወሊድ በኋላ አብዛኞቹ ሴቶች ወደ ሥራ የማይመለሱ መሆኑ፣  በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ላይ የተመለከተው የዝቅተኛ ደመወዝ ወሳኝ ቦርድ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ አለመደረጉ በድኅረ ክትትሉ የተለዩ እና ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሌሎች ዋና ዋና ግኝቶች ናቸው፡፡ 

የኢሰመኮ የሴቶችና ሕፃናት መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ላምሮት ፍቅሬ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በኮሚሽኑ የክትትል ግኝቶችና በውይይት የተገኙ ግብዓቶችን መነሻ በማድረግ በቀጣይ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል። አክለውም በሕግ የተቀመጡ የሴት ሠራተኞች መብቶችን ማክበር፣ ማስከበር እና ማሟላት ላይ ትኩረት በመስጠት ባለግዴታ አካላት ከተሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት በመነሳት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አድርገዋል።

በተካሄደው የምክክር መድረክም በክትትሉ ግኝቶችና ምክረ ሃሳቦች መሠረት በቀጣይ እያንዳንዱ ባለግዴታ አካላት መሥራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ የወደፊት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በዚህም መሰረት በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚሠሩ ሴት ሠራተኞች መብቶች አያያዝን ለማሻሻል የሠራተኞቹ የመደራጀት መብት ሕጉን እና ሥርዓቱን ተከትሎ በተሟላ ሁኔታ እንዲከበር፣ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በተዋረድ የሚገኙ ቢሮዎች በፓርኩ ውስጥ በሚገኙ ፋብሪካዎች ላይ ተገቢ የሆነ መደበኛ ቁጥጥር ለማድረግ እና እርምት ለመውሰድ የሚያስችል አሠራር መዘርጋት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ላይ የተመለከተው የዝቅተኛ ደሞዝ ወሳኝ ቦርድ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ በማድረግ የሴት ሠራተኞች በቂ ክፍያ የማግኘት መብት ላይ ያላቸውን የመደራደር አቅም ማሳደግ እንደሚገባም ተገልጿል። 

በተመሳሳይ መልኩ ባለግዴታ አካላት የቁጥጥር መስፈርቶችን በማዘጋጀት የሥራ መደቦቹ የሚያስፈልጋቸውን የደኅንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶችና ሌሎች ተጨማሪ ድጋፎች በመለየት የቁጥጥር ሥራ መሥራት እንዳለባቸው፣ ሴት ሠራተኞች የወሲባዊና ሥነ ተዋልዶ ጤና መብቶችን የሚመለከቱ መረጃዎችና አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለሁሉም ሴት ሠራተኞች ስልጠና የሚያገኙበት አሠራር መዘርጋት እንዳለበት ተገልጿል፡፡ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶች ተደራሽነትን ማረጋገጥ፣ የነፍሰ ጡር እናቶች የጤና ክትትልን ማሻሻል፣ የወለዱ እናቶች ሥራቸውን የሚያቋርጡበትን ምክንያት በተመለከተ በባለግዴታ አካላት ጥናት መደረግ እንዳለበት እና በአጠቃላይ የሴት ሠራተኞችን መብቶች አያያዝ ለማሻሻል ባለግዴታ አካላት ሰፊ ሥራ የሚጠበቅባቸው መሆኑን አጽንዖት በመስጠት የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Location Ethiopia

Related posts

January 25, 2022August 28, 2023 Quiz
ስለ ትምህርት ሰብአዊ መብት ምን ያህል ያውቃሉ?
January 11, 2022August 28, 2023 Quiz
ስለ ሰብአዊ መብቶች ምን ያህል ያውቃሉ?
March 14, 2022March 14, 2022 EHRC on the News
Ambush and reprisals in Ethiopia kill 64 - rights body – Reuters
June 17, 2021July 14, 2021 EHRC Quote
IPC findings underscore dismal humanitarian situation in Tigray

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on TwitterYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on Linkedin

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
EHRC
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org

© 2023 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Women’s & Children’s Rights
    • HR Monitoring & Investigation
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter YouTube Linkedin Flicker
 

Loading Comments...
 

    Search
    Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
    Powered by  GDPR Cookie Compliance
    Privacy Overview

    This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

    Strictly Necessary Cookies

    Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

    If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.