የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 13 

ማንኛውም ሰው የመማር መብት አለው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት መማር ግዴታ ሊሆንና ለሁሉም ሰው በነጻ ሊሰጥ ይገባል።

ትምህርት ለሁሉም ዓለም አቀፍ መግለጫ፣ አንቀጽ 3 (1 –2) 

ለትምህርት ሁለንተናዊ ተደራሽነት እና ፍትሐዊነት መስፋፋት፦

  • መሠረታዊ ትምህርት ለሁሉም ሕፃናት፣ ወጣቶች እና ጎልማሶች መሰጠት አለበት። ለዚህም መሠረታዊ የትምህርት አገልግሎት ጥራትን ማስፋት እና ልዩነቶችን ለመቀነስ ተከታታይ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው።
  • መሠረታዊ ትምህርት ፍትሐዊ እንዲሆን ሁሉም ሕፃናት፣ ወጣቶች እና ጎልማሶች ተቀባይነት ያለው የትምህርት ደረጃ እንዲያሳኩ እና እንዲጠብቁ ዕድል ሊሰጣቸው ይገባል።

The Right to Access to Education